ቅኔ.1

እኛን ሲሉ መጥተው  አትጨክኑባቸው

ማርካችሁ ገፋችሁ ባዶ አታስቀሯቸው

               ነጋድራሰ ተሰማ እሸቴ

 

 

ቅኔ.2

እነኝህ ፋሽሽቶች በውነት የዋህ ናቸው

የአክሱምን ሀውልት ሮም መውሰዳቸው

 የመርዙ ምልክት እንዳይሆንባቸው

             ነጋድራሰ ተሰማ እሸቴ

 

 
ቅኔ.3

የኔታ አካለወርቅ ትምህርት ሚኒስቴር

አልማዝ ወርቅ የሚገኝ መሆኑን ከምድር

መጽሀፍ ዘርግቶ እንደማስተማር

 እኔን ተከትሎ ይላል ብር ብር

           ነጋድራሰ ተሰማ እሸቴ

 
ቅኔ.4

                    

ባዲሱ መሳሪያ በመስኮቦች እቃ

ትስቅብናለች ጎኗን ተጠብስቃ

         ነጋድራሰ ተሰማ እሸቴ

 

 
ቅኔ.5

 

ጨክኖ ለመግደል ሆዴ አልችል አለ እንጂ

አላማማ ምነው የነፍጠኛ ልጅ

         ነጋድራስ /ተ/እ

 

 
ቅኔ.6

     

አለም ሲደላደል ሲከፋፈል በእጣ

የኢትዮጵያ አርበኛ ኤርትራን አወጣ

               ነጋድራስ /ተ/እ

                                 

 
ቅኔ.7

 

ሀበሾች አያውቁኝ ምን አስወቀሰኝ

አሜሪካ እያለ ሰርቶ እሚያፈርስኝ

            ነጋድራስ /ተ/እ

 

 
ቅኔ.8

 

አዳራሹ   ሰፊ በሩ አልጠበባችሁ

በተራ በተራ ምነው መግባታችሁ

              ነጋድራስ /ተ/እ

 

 
ቅኔ.9

 

አሻግራቸውና ከብቶቻችን ይብሉ

ያ ሳር አይደለም ወይ የምናየው ሁሉ

              ነጋድራስ /ተ/እ

 

 
ቅኔ.10

 

ያራዳ ሴት ሁሉ ዘመድም የለሽ

ለፈታሽ ነገርኩት እኔ ላገባሸ

             ነጋድራስ /ተ/እ

 

 
ቅኔ.11

  

ሞጣ ቀራኒዮ ምነው አይታረስ

በሬ ሳላይ መጣሁ ከዚህ እዚያ ድረስ

 

 
ቅኔ.12

 

እውቀቱ ሳያንሰው ሳይቸገር ሃብት

ፍቅር ተጠናውቶት ከድሃ ባልቴት

 ታዬ ተኮራምቶ ጠባብ ክፍል ቤት

                        በ ሳ/አ 

 

ቅኔ.13

 

ምነው እዚያ ማዶ ጭር አለ ሰፈሩ

ምነው እንዲህ ውዲህ ስዎች አይጣሩ

ለካ ቋንቋ አጥሮት ነው አገሩ መንደሩ

                           በሳ/አ

 
ቅኔ.14

ባሌ መለሎ ነው ብዬ ሲያቀብጠኝ

ድንገት መንገድ ታዬ ጉድ አደረገኝ

መዋረዴ አልቀረ አላመለጥኩኝ

መለስተኛ ነው ወይ ብለው ጠየቁኝ

                          በሳ/አ

 
ቅኔ.15

አልጫን ብትለው ዱር ለምዳ አህያው

ሁሉን እይው ብሎ ልጓሟን ፈታው

ያዳኙን ጭካኔ ተንኮሉን አይታው

መሆኑን አመነች አማራጭዋ ሰው

                       በሳ/አ

 
ቅኔ.16

አህያ ይሉታል የናቁትን ሰው

የደደብ ተምሳሌት እኔን አድርገው

በጀርባዬ አይደል ወይ አገር ያቀናሁት

ምነው ስሜን እንዲህ ለውርደት ዳረጉት

                       በሳ/አ

 
ቅኔ.17

ማእበል አናውጦት ሸቀጡን ቢያጥበው

ቀይ ባህር ነጋዴው ክስረት ገጠመው

ዘንድሮ ምን ሆነ ምን ጉድ አገኘው

ዋናተኛ ሆኖ ሲያተርፍ ስናቀው

                   በሳ/አ

 
ቅኔ.18

 

ለሙግት ለፍልሚያ ቀን ሳይቆርጡለት

ድንገት ከጎን ደርሰው ነጠቁት እርስት

                   በሳ/አ

 

 
ቅኔ.19

 

ልሞ የተፈጨ የደቀቀቅ ጤፍ ነው

ተገረዳደፈ  የሚለኝ ሰው ማነው

           (ደራሲው የማይታወቅ)

 

 
ቅኔ.20

             

ለኔ የሚታየኝ ስላልታያችሁ

እረ እናተ ሆዬ ሳቅ ሞትኩላችሁ

           ነጋድ/ ተሰማ እሸቴ

 

 
ቅኔ.21

            

መለኛው መምሬ ሙሉ አለሙን ቀጭቶ

አዲስ ጸጋንና ታምራትን ትቶ

ያመነዝር ጀመር ዳዊቱን አንግቶ

                   በሳ.አ