Articles                                                 መጣጥፍ

  Back Home      Articles          Poems           News              Jokes               Email Us

        THIS WEBSITE IS CURRENTLY BLOCKED IN ETHIOPIA

በውጭው አለም ያለው የትግራይ ተወላጅ  ዝምታ
ሲያቃጥል በማንኪያ  ሲቀዘቅዝ
በእጅ ይመስላል።
ገጽ = 2   =

      
  

በውጭው አለም ያሚገኘው የትግራይ ተወላጅ ሌላው ቀርቶ በትግራይ ያሉት ወገኖቹና ቤተሰቦቹ በወያኔ አፈሙዝ አፋቸው መለጎሙ እንጂ ወያኔን እንደማይደግፉ እንኳ ለሌላው ህዝብ አይናግርም።የትግራይ፡ሕዝብ፡በወያኔ ደረሰበት የሚባል አንድም በደል ሲጠቅሱ አይሰሙም።

 የትግራይ ሕዝብ ዝምታ ምክንያቱ ምንድነው? የሚልና የሚጠይቀው ሌላው ህዝብ! ለዝምታው ምክንያት መታፈኑ መሆኑን የሚመሰክረው ሌላው ህዝብ!  

ለመሆኑ እኛው ጠይቀን እኛው መስክረን እንዘልቀዋለን እንዴ?


ሃቁን መናገርና እውነታውን መቀበል ሃገር ይከፋፍላል በሚል ስጋት የሌለና የማይጨበጥ ምክንያት እየሰጠን ለምን እራሳቻንን እናታልላለን።  ሃገርም የሚከፋፈል ከሆነ ሳናስብበት በሽፍንፍን እየሄድን ድንገት ከሚከፋፈልና ዱብ እዳ ከሚሆንብን እውነታውን ግልጽ አድርገን ስለተከታዩ መከፋፈል ማሰብ ይሻላል። አልያ ለትግራይ ህዝብ በወያኔ መበደል ከትግራይ ህዝብ የበለጠ ሊመሰክር የሚችል የለምና ቀደም ቀደም እያልን የምንሰጠው ምስክርነት የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ እንዲሉ ይሆንብናል።

በውጭው አለም ያለው የትግራይ ተወላጅ በትግራይ ያሉትን ቤተሰቦቹን መበደል መናገርና መመስከር ብሎም በገሃድ መቃወም ካልፈቀደ አንድም የትግራይ ህዝብ አልተበደለም ወይም አልታፈነም ማለት ነው።አልያም በውጭው አለም ያለው የትግራይ ተወላጅ  የቤተሰቦቹን መበደል በመናገር ወያኔን እንዳያጋልጥ ጥንቃቄ የሚያደርግ ወያኔ ነው ማለት ነው።

ከዚህ ውጭ ምንም የሚሆን ነገር የለም።

የትግራይ ህዝብ ከወያኔ እንደሚለይ ሊያስረዳ የሚገባውም የትግራይ ተወላጅ እንጂ ሌላው ኢትዮጵያዊ ሊሆን ከቶውኑ አይቻለውም። ይህን ስል    ሌላው ኢትዮጵያዊ የትግራይ ህዝብ ከወያኔ እንደሚለይ የራሱ ግንዛቤ ሊኖረው አይችልም ማለቴ ሳይሆን! ስለ ጎይቶም ማንነት ከጎይቶም እንጂ ከጨቡዴ ልንሰማ አይገባንም ለማለት ነው። ጎይቶም ማንነቱን መግለጽ ካልፍለገ ማንነቱ ይፋ እንዲሆን አልፈለገምና ድብቅነቱን  እንጂ በጨቡዴ የሚዘረዘረውን የጎይቶምን ማንነት መቀበል አይቻልም ነው የምለው። ባይሆን ጎይቶም እራሱን ግልጽ ካደረገ በህዋላ የጨቡዴ ማብራሪያ አባሪ ማስረጃና ምስክር ሆኖ የጎይቶምን ምንነት የበለጠ እንዲያሳይ ይረዳል።

እንደኔ ግምት የትግራይ ህዝብ ከ 90% በላይ ወያኔን ይደግፍ የነበረና በአሁኑ ሰአት ግን በወያኔ ተደጋጋሚ ኢ-ሰባዊ ጭፍጨፋ ሳቢያ አብዛኛው የትግራይ ሕዝብ ለፋሽሽቱ ለወያኔ ድጋፍ መስጠት ከሌላው ህዝብ ጋር ጥርስ እንደሚያናክሰውና ደም እንደሚያቃባው በመገመት ዝምታን መርጥዋል። ወያኔን ሙሉ ለሙሉ እንዳይቃወምና ከሌላው ህዝብ ጋ እንዳይሰለፍ ደግሞ ምናልባት ወያኔ በመንግስትነት የመቀጠል እድል ካለው ሊያደርስበት የሚችለውን ቅጣትና ጥቃት በማሰብ ሲያቃጥል በማንኪያ ሲቀዘቅዝ በ እጅ እንዲሉ ቁርጡ እስኪለይ ጥግ መያዙን መርጧል፡፤ ወያኔ የህዝብን አመጽ ለማፈን ከቻለና በመንግስትነት ከተረጋጋ  እሰየው ነው በቀላሉ "ከበሮውን በትከሻው አንገት አድርጎ   ሰማይ ደርሶ እይፈረጠ " ናይ...ወያኔ..ሰራዊት...ደምሲሲሎ  ካብ ነፍጠኛ ትዕቢት" (የቁጩ ትግሬኛ ነው)እያለ ደስታውን በመግለጽ ይገላገለዋል።

ወያኔ የማይቀረው ግብአተ ሞቱ እንዳይነሳ ሆኖ ሲፈጸም ደግሞ! ከበሮውን አንግቶ እየደለቀ ባይዘልም እንዳሁኑ በዝምታ መቀመጥ እንደማያወጣ ተረድቶ በህዝባዊ ድል በአሉ ላይ ቀድሞ በመድረስ የህዝብ ወገን ኢትዮጵያዊነቱን ያረጋግጥ ይሆናል። ያ ነው እንግዲህ ሲያቃጥል በማንኪያ ሲቀዘቅዝ በእጅ የሚባለው። የግል አመለካከቴ ነው። በተለይ እናንተ  የትግራይ ህዝብ ከወያኔ መለየቱን ከባለቤቱ በላይ እናውቃለንና እንመስክር የምትሉ ቡዶች መቼም እንደማታስተርፉኝ አውቃለሁ። እኔ ግን ከናንተ አይነት 1000 የ ሪሞት ምስክርነት ይልቅ  የትግራይ ተወላጅ አንድ ኦርጅናል ምስክርነት ብሰማ እመርጣለሁ!!!

ይልቅ እንቅጩን ነግረናቸው ዛሬ አውቀው የሚያጠፉ ሁሉ ነገ የይቅርታው በር እንደሚከረቸምባቸው በማስጠንቀቅ እርምት እንዲወስዱ ማድረግ እንጂ ለነሱ ጥፋት እኛ ኤክስኪውዝ እያዘጋጀን ሁለተኛ ጥፋት ባንፈጽም ጥሩ ይመስለኛል።እያልኩ በሚከተሉት ስንኞች ልሰናበት
                             የቡሬ ጥጃ አባቱ ሁለት
                             ከጥቁሩ ያድራል ዳልቻው ሲሞት

                           
ቸር ይግጠመን!!

ደብተራው ዘጨርቆስ