Articles                                                 መጣጥፍ

  Back Home      Articles          Poems           News              Jokes               Email Us

        THIS WEBSITE IS CURRENTLY BLOCKED IN ETHIOPIA

በውጭው አለም ያለው የትግራይ ተወላጅ  ዝምታ
ሲያቃጥል በማንኪያ  ሲቀዘቅዝ
በእጅ ይመስላል።

     
በርግጥ ወያኔ የተፈለፈለው ያደገውና  ለአቅመ - ሳጥናዔልነት የደረሰው  በትግራይ ህዝብ ጉያ ነበርና የጨ ቅላ እድሜው ምኞትና ግብም ከትግራይ ጠባብ ጓዳ ያልዘለለ የዛው በዛው ሥሬት እንደነበር  የቅርብ ግዜ ባንለውም ትዝታው ግን አሁንም ድረስ ሕያው ነው፡፤

ለበትረ ስልጣን ከመብቃቱ ጥቂት አመታት በፊት ጀምሮ እስካሁን ያለው የወያኔ ሕይወት ግን ከትግራይ ጠባቧ ጓዳ አልፎ በሰፊዋ በኢትዮጵያ ማጀት እየተንቧቸበት ይገኛል፡፤ የተመኙትን መሆንና ማግኘት ቃላል ባይሆንም ቅሉ ጥረትና ግረት ከታከለበት የማይቻል አይደለም። ከምኞት በላይ ለማግኘት ግን ከጥረትና ድካም በላይ እድል ያስፈልጋል። አዎ ወያኔዎች እድልኞች ናቸው የሚባለውም ለዚህ ነው፡፤ ትግራይን አስለቅቀው በር ቆልፈው ለመኖር አልመው ጫካ የገቡት መስራቾች እንደ አሳ ዘር እተዋዋጡም ቢሆን ዛሬ ያሉበት ቦታ የደረሱት በእድል እንጂ በጉብዝና ወይም እነሱ እንደሚነግሩን በጀግንነት አይደለም፡፤ ይህን ያልኩበት ምክንያት ማብራራት የአንባቢንም የኔንም ግዜ  ማባከን ይሆናልና ይልቅ ወደ ዋናው የጽሁፌ አላማ ልቻኮል፡፤

አዎ ወያኔ ዛሬ መላው ኢትዮጵያን እያመሰ ይገኛል፡፤ወያኔነትም ዛሬ በትግራይ ብሄር ብቻ ሳይወሰን በየብሄሩ  ተቀፍቅፎ{ የእገሌ ብሄር.... ዴሞክራሲያዊ ድርጅት} ወይም ዴ.ድ በሚል መጠሪያ  ተፈልፍሎ  እንደ ለሃጫም ትል የታከከውን ሁሉ እየመረዘ ድፍን አገሪቷን እያመሰ ነው።

ዛሬ ወያኔ ስንል በጥቂት መርዘኛ እባቦች የሚነዳ የጅብ መንጋ ማለታችን እንጂ! እንደ ድሮው ከትግራይ ህዝብ ጉያ የተፈለፈሉ ጥቂት ጥፉ ዘሮች ብቻ ማለት አይደለም፡፤ የጅቦቹን መንጋ የሚነዳው እባቡ ክፍል  በአንድ ዘር ብቻ የተማከለ ቢሆንም ቅሉ ቀሪው ታጋጅ መንጋ ያማከለው  በሆዳምነት ባህሪ እንጂ በዘር አለመሆኑን የክልል ሶስቱን ጅብ አውራ አዲሱ ለገሰንና የክልል አራቱን አባ ዱላን መጥቀሱ በቂ ይመስለኛል፡፤

ይህ በሆዳምነት ባህሪ ላይ ተመርኩዞ በየክልሉ የተቀፈቀፈው የእባቡ ክፍል እንቁላል ሰላማዊውን ኢትዮጵያዊ ለ14 አመታት ሲያስቃይና ሲግጥ ኖሮ ዘንድሮ ቅንጅት የሚባል ለመርዙ ማርከሻ መድሃኒት ሲገኝለት ከእንግዲህ ቅፍቅፋቸው ህይወት እንደማያገኝ የተረዱት እባቦች መድሃኒቱን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ሩጫ ይዘዋል፡፤ ይሁን እንጂ መርዙ ያስቃየው ዜጋ ሁሉ መድሃኒቱን ይሻልና ከቶውንም ሊያጠፉት እንደማይቻላቸው መርዝ እንጂ እሳቤ መሰለቅ የማትችለው ትንሽዋ የእባብ አይምሯቸው ልትረዳ አልቻለችም፡፤ሆድ እንጂ እራስ የሌው የጅብ መንጋ ይህን ሊረዳ እንደማይችል ይታወቃል።

እንግዲህ አሁን የምንገኝበት ሁኔታ ይህን ይመስላል፡፤ ሰላማዊው ሕዝብ እንደ እባቦቹ ዘርም ሳይለየው እንደ ጅቦቹ ባህሪ (ሆዳምነት) ሳይከፋፍለው ድምጹን ከፍ አድርጎና እጅ ለ እጅ ተያይዞ እየጮህ ይገኛል፡፤ ይሁን እንጂ እባብ ደንቆሮ ነውና ጩሀቱን አይሰማም። ሆዱ የሞላ ጅም ደግሞ የራሱ ጩህት እንጂ በጆሮ ግንዱ የሚያስተጋባው ሌላ ድምጽ ሊሰማ አይችልም።ህዝቡ ግን በቃኝ ብሎ ተነስቷል።

ባደባባይም ብሶቱንና እሮሮውን በገሃድ ይገልጻል፡፤ የእባቦቹ መፈልፈያ ምድር ከሆነቺው ከትግራይ በስተቀር በሌላው ክልል ያለው ህዝብ ሁሉ ያለ ፍርሃት እባቡን ከነ መንጋ ጅቦቹ ለማጥፋት መቁረጡ በድፍረት ይናገራል! በድፍረት ይጋፈጣል!! በትግራይ ክልል ጩሀቱ የማይሰማበትን ምክንያት የተለያየ ምክንያት ሲሰጡ አስተውያለሁ። ገሚሱ የትግራይ ሕዝብ ላም እሣት ወለደች እንዳትልሰው እሳት እንዳትተወው ደግሞ ልጅ ሆነባት እንዲሉ ሆኖበት ነው ይላል፡፤ገሚሱ ደግሞ  የእባቦቹ መርዝ እንደ ትግራይ ህዝብ የጎዳው የለም የመርዙ አስኳል የሚያርፈው ትግራይ ሕዝብ ላይ ነው! የትግራይ ህዝብ እንደሌላው ሕዝብ የፈውሱን መድሃኒት እንኳ እንዳያገኝ ተከልክሎ  በመርዙ ብዛት ልሳኑ የተዘጋ ድምጽ አልባ ሆኗል፡፤ ይላል።

ለትግራይ ህዝብ መበደል ምስክርነት የሚሰጠው ሌላው ሌላው ሕዝብ እንጂ! ከወያኔ ቁጥጥር ውጭ በውጭው አለም የሚገኘው የትግራይ ተወላጅ በትግራይ የሚገኘው ቤተሰቡ በወያኔ እባቦች ይደለልም ይበደልም ምንም የሚተነፍሰው ነገር የለም ፡፤ ብቻ ዝምታ!!

አንዳንዱ ኢትዮጵያዊ  ደግሞ በተለይ በውጭው አለም ያለው። ይናደድና። ለመሆኑ በትግራይ ያለው የትግራይ ተወላጅ ዝምታ ምክንያት ጉያው የተወሸቀውን  ወያኔን ፈርቶ ነው! እንበል በውጭው አለም ያለውስ ለምን ዝም ይላል? የሚል ጥያቄ ያነሳል፡፤

ሌላው አንድነት ናፋቂ ይነሳና በተራቀቀ አባባል እዚህ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል!! ይላል!!!(ሌላው ደግሞ "ድንቄም ጥንቃቄ ሲተኩሱ ነው ሲናገሩ መጠንቀቅ ያሚያሻው"" ይል ይሆናል።  ) እሱን ችላ ብሎ  የትግራይን ህዝብ ከወያኔ ለይተን ማየት አለብን ብሎ! የትግራይን ህዝብ ኢትዮጵያዊነት አድምቆ ይናገርና! በትግራይ የሚገኘው ህዝብ እንደሌላው ህዝብ እንኳ መናገር የማይችል መሆኑን እያብራራ ይደሰኩራል።ፍየል ወዲህ ቅዝም ዝም ወዲያ! ይልዋል ይሄ ነው። በውጭው አለም ያለው የትግራይ ተወላጅ ለምን ዝም አለ እንጂ ጥያቄው በመቀሌና በአድዋ ስላለው ሕዝብ ማን ጠየቀ?

ይህ የኔም ጥያቄ ነው! አዎ በውጭው አለም ያለው የትግራይ ሕዝብ ወያኔን በግልጽ አይነቅፍም፤ የተቃውሞ ሰልፍም አይወጣም፡፤ለምን? ይህን መመለስ ያለበት እንደኔ እንደኔ የትግራይ ህዝብ እንጂ ሌላው ሕዝብ አይደለም፡፤ በጣት የሚቆጠሩ የትግራይ  ተወላጆች ወያኔን በግልጽ ቢቃወሙም ከብዛታቸው አንጻር ግን ሊጠቀሱ የሚገቡ አይሆኑም።

ይህ ጥያቄ በኔ አመለካከት በውጭው አለም የሚገኘው የግትራይ ሕዝብ ወያኔን እንደ ሂሮ የሚመለከት እንጂ ጭራሽ የሚጠላበትና የሚቃወምበት አንጀት አለው ብዬ አላስብም፡፤ስለዚህ በዲያስፖራው ያለውን የትግራይ ህዝብ ከወያኔ ነጥሎ የሚያይ አይን ከቶውንም ሊኖረኝ አይችልም።

                                              ወደ ገጽ 2