Articles                                                 መጣጥፍ

  Back Home      Articles          Poems           News              Jokes               Email Us

        THIS WEBSITE IS CURRENTLY BLOCKED IN ETHIOPIA

የኖርወይ መንግስት ስደተኞውን አስገድዶ
ወደ ኢትዮጵያ እንደማይመለስ ቃል ገባ

 

አፍተን ብላደት በመባል የሚታወቀው የኖርወይ ጋዜጣ በ 27.10.05 ባወጣው እትሙ ላይ የኖርወይ መንግስት የኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን የጥገኝነት ማመልከቻ በአዲስ መልክ እንደገና እንዲታይ መወሰኑን አስታወቀ::

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በዉጭ አገር እንደ ሰደድ እሳት በመቀጣጠል ላይ የሚገኘውን የተቃዋሚ ኅይሎች እንቅስቃሴ ለማዳፈን ሲሉ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን መቀበል እንደሚፈልጉ እና ወደ አገራቸውም እንዲመለሱ ተስማምተው መሄዳቸው ይታወቃል::

ኢትዮጵያ በውጭ አገር ከሚኖሩ ስደተኞች ቢያንስ ከ 400 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደምታስገባ በጥናት ተደርሶበታል ይህም ገቢ አገሪቱ ከቡና ወይም ከሌላ ምርት ሽያጭ ከምታገኘው በልጦ ተግኝታል፣ ከ 70 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ያላት አገር ኢትዮጵያ አብዛኞቹ ህዝቦቻ ኑራቸው ከጅ ወደ አፍ ከመሆኑም በላይ በየጊዜው በርሃብና በበሽታ የሚያልቀው የህዝብ ቁጥር ቀላል አይደለም::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሳሰባቸው የ አገር ወይም የህዝብ ጉዳይ ሳይሆን ስልጣን በ እጃቸው እንደያዙ መቆየት ብቻ በመሆኑ ለስደተኞውም ሆነ ለህዝቦቻ አላሰቡላቸዉም::

ቁጥራቸው 300 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ተወስኖ ዝርዝራቸውም ተዘጋጅቶ ነበር ከእነዚህም ውስጥ አንዳንዶቹ  እስከ 9 አመታት የቆዩ እንደሚገኙበት ታዉቃል፣

ከኖርወይ የሰራተኞና የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት ሄልጋር ላንገላንድ እና ማግንሂልድ መልትቫይት የተባሉት ባለስልጣናት እንዳስታወቁት ከ እንግዲህ ወዲያ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከሚኖሩበት ቦታ ተገደው መንገድ ላይ እንደማይጣሉ አስፈላጊው የምግብ  የመጠለያና የህክምና እርዳታ እንደሚደረግላቸው የፖለቲካ ችግር ያለባቸውን ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ ለግርፋትና ለእስራት እንደማይላኩ ጋዜጣው ገልጾታል::

ያራ ተብሎ የሚጠራው የማዳበሪያ ሻጭ ድርጅት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን የ አሻሻጭነት ኮሚሽን በሽልማት መልክ ለመስጠት በጋበዘበት ወቅት፣ ይህ ሽልማት የራሱን ህዝብ በአደባባይ ትዕዛዝ በመስጠት ላስጨፈጨፈ አማባገነን መሪ እንዳይሰጥ ለመከራከር የተቃቃመው የፀረ ያራ ሽልማት ኮሚቴ ባደረገው የተቀነባበረ ስልታዊ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ዘመቻ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖርወይ ጠቅላይ ሚኒስትርም፣ ሆኑ ሌሎች ማንም ሚኒስትር ባልተገኘበት ሁኔታ የተሰጣቸውን ኮሚሽን ተቀብለው እንዲመለሱ ያደረጋቸው መሆኑ ዪታወሳል፣ ይህ ጉዳይ ከዲፕሎማሲ አካያ ሲታይ ማንም ሚኒስትር ወይም ባለስልጣን ሳይቀበላቸው እንደ ተራ ሰው ኖርወይ ገብተው መውጣታቸው በጣም አሳፋሪና ጠቅላይ ሚኒስትሩን  እርቃናቸውን ያስቀራቸው ጉዳይ ነው::

በኖርወይ የፀረ ያራ ሽልማት ኮሚቴ፣ የስደተኞች ኮሚቴ፣ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ሌሎችም የአገርና ህዝብ አፍቃሪዎች የትግል አቅጣጫቸዉን በማስፋፋት አቶ መለስ በስደተኞው ህይወት ላይ ሸርበውት የሄዱት ሴራ መክሸፍ ስለነበረበት በተከታታይና ባለተቃረጠ መልኩ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ለኖርወይ መንግስት በማስረጃ ለማስገንዘብ ችለዋል፣ በኖርወይ ያሉ መላው ኢትዮጵያዊያንም ከዳር እስከዳር በመተባበር አንድ ላይ ተሰብስቦ መፍትሄ በመፈለግ ያለማቃረጥ ሰላማዊ ሰልፍ በማዘጋጀት የመለስ መንግስትን ገዳይነትና ፋሽስታዊ አገዛዝ በሰላማዊ ሰልፎች በጹህፍና በስብሰባዎች የተደረጉት ጥረቶች ሁሉ ተደምረው ዛሬ ሊመለሱ የነበሩ ስደተኞች ጉዳይ እንደገና እንዲታይ በመወሰኑ እንካን ደስ አላችሁ የወያነ/ኢሃድግ ደጋፊዎችም የፖለቲካ ሽንፈታችሁንና የሀፍረት ሸማችሁን ተከናነቡት ትግላችንም ስልጣን በህዝብ ለተመረጠ ዲሞክራሲያዊ መንግስት እሰከምታስረክቡ ድረስ ይቀጥላል::

በኖርወይ የመለስ ፖለቲካ ለሁለተኞ ጊዜ እርቃኑን በመቅረቱ ልንበረታታ የሚገባ ሲሆን ወደፊትም ይህ ትብብራችን ከቀጠለ ከምንፈልገው ውጤት እንደርሳለን::

 

መሀመድ በሽር