የኢ.ህ.አ.ፓው መሪ የሜልበርን ቆይታ


 

ረዥም አመታት የኢሕኣፓን የትግል እንቅስቃሴ በመምራት፥ በካበተ የትግል ልምዳቸውና ጥንካሬያቸው የሚታወቁት አቶ መርሻ ዮሴፍ በአውስትራልያ ሜልበርን በመገኘት ከኢትዮጵያዊው ወገን ጋርኘ የሃሳብ ልውውጥ አድርገዋል።

 ጁን 8 ቀን እሁድ ከምሽቱ ሁለት ሰአት ጀምሮ በተካሄደው በዚህ ውይይት ተጋባዥ እንግዶች የድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች የተሳተፉበት ነበር። የውይይቱም መንፈስ መግባባትና መደማመጥ የሰፈነበት ከመሆኑም በላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ቆም ብሎ ስለሃገሩ ወቅታዊ ሁኔታና ብሎም መጭ ራዕይ የማሰብ ግዴታ እንዳለበት ግንዛቤ ያስጨበጠ ነበር።

 ስብሰባው የተጀመረው አቶ መርሻ ዮሴፍ በሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ዙሪያ በማተኮር ባቀረቡት ማብራሪያ ነው። አቶ መርሻ ትኩረት የሰጡባቸው ርዕሰ ጉዳዮች  1ኛ ስለ ኢሕኣፓ የትግል እንቅስቃሴ 2ኛ ስለ ሃገራችን ወቅታዊ ሁኔታ 3ኛ በቅርቡ የምስረታ ስብሳባ እንደሚያደርጉ የሚጠበቁት ኢሕኣፓን ጨምሮ ከ 16 ያላነሱኘ ተቃዋሚ ድርጅቶች ስለሚመሰርቱት የሕብረት ግንባር በተመለከተ ነበር።

 ኢሕኣፓ ከምስረታው ጀምሮ ያደረጋቸውን እንቅስቃሴዎች፥ የከፈላቸውን መስዋእትነቶች፥ ጠቀስቀስ አድርገው ያለፉት አቶ መርሻ ፥ በኢሕኣፓ የተፈጸሙ ስህተቶችንም በግልጽ ከማስቀመጥ አልተቆጠቡም። ምንም እኳን አሉ አቶ መርሻ፥ኘ ምንም እንኳን በወያኔ የሚመራው መንግስት በሃገቤት ገብተን ታግለን የማተገል መብታችንን ቢንፍግናኘ በድርጅታችንም ላይ ለአለፍት 11 አመታት ሲያደርስ የቆየውና እያደረሰም ያለው እመቃ እንደ ልብ ተንቀሳቅሰን የቆምንለትን አላማ በሚፈለገው መጠንና ፍጥነት እንዳንተገብር እንቅፋት መፍጠሩ እውነት ቢሆንም ኢሕአፓ ያለ አንዳንች መንበርከክ፥ አቅምና ሁኔታዎች በፈቀዱለትና ባመቹት የትግል ስልቶች ሁሉ በመንቀስቀስ ላይ ይገኛል። ካሉ በኋላ በመቀጠልም ለዚህ አባባላቸው መገለጫ ሲያስቀምጡ

 ኢሕኣፓ የወያኔ አፈናና ክትትል በሃገር ቤት እንቅስቅሴ ለማድረግ አያመችም ብሎ አልተቀመጠም። ከግዜ ወደግዜ እየጠነከረ ያለ እንቅስቃሴ በሃገርቤትም እያደረገ ነው። ኢህኣፓ የወያኔ አፈናና ግድያ ባለበት አካባቢ በህቡ፥ እንዲህ ደግሞ ሰላም በሰፈነበት በውጭው አለም ደግም በግልጽ መድረክ ከሕዝብ ጋር በመገናኘት አላማውን ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራ ያለ ድርጅት ነው።በማለት ስለ ድርጅታቸው የቃረቡትን አጭር መግለጫ ቋጭተው ወደ ሁለተኛውና የወቅቱን የሃገራችንን ሁኔታ ወደ ዳሰሰው ርዕሰ ጉዳይ አምርተዋል።

 በአሁኑ ወቅት ሃገራችንና ሕዝባችን አሉኘ ምሬትና ቁጭት በታየበት አገላለጽ፥ የዲሞክራሲያዊ መብቶች አለመከበርና ከዚሁ ጋር በተዛመደ እየደረሰ ያለው ግፍ ሳይያንስ በኤድስና በርሃብ እንደ ቅጠል እየረገፈ የሚገኝበት አሳሳቢነቱም ከመቼውም ግዜ በከፋ የታሪክ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። በማለት ቀጥለውም የወያኔ መንግስት በሕዝባችን ላይ እያደርሰ ያለውን በደል በዝርዝር አቅርበዋል። የስብሰባው ተሳታፊ ወገን አቶ መርሻ በመግለጫቸው የዳሰሷቸውን ጉዳዮች ሙሉ በሙሉ ባንክሮ የተከታተለ ሲሆን በተለይ የብዙውን ትኩረት የሳበው ራዕይ አጥቶ ለቆዘመ ኢትዮጵያዊ ወገን የምስራች የሆነውን የተቃዋሚዎችን ሕብረት በተመለከተ ያቀረቡት ማብራሪያ ነበር።

ላለፉት 11 አመታት ተቃዋሚ ድርጅቶች አብረው ለመስራት ባለመቻላቸው ኢትዮጵያዊው ሁሉ እንዳዘነና እንዲያውም ወይ ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ የሚል መልዕክት አዘል የምሬት ቃል እስከ መሰንዘር መድረሱን አቶመርሻ አስታውሰው። ይህ እንዳይደገም ድርጅታቸው ከየትኛውም ተቃዋሚ ድርጅት ጋር ግንባር ፈጥሮ ለመስራት የሚጥር መሆኑን ቃል ገብተዋል። ኢሕኣፓ ባሁኑ ወቅት ከኦነግም ጋር ግንባር ፈጥሮኘ ለመስራት ጥረት እያደርተገ መሆኑን ገልጸው፥ እያንዳንዱ ተቃዋሚ ድርጅት በተናጥል የሚያደርገው ትግል የትም እንደማያደርሰው ከአለፉት 11 አመታት እንቅስቃሴ ልምድ የቋጠረበትና ጠንቅቆ የተረዳበት ምዕራፍ ላይ ስለሚገኝ የሚፈጠረውም ሕብረት በዚሁ ልምድ የዳበረ፥ የጠነከረ፥ መቻቻልና መግባባት የሚሰፍንበት እንደሚሆን ያላቸው ተስፋ ክፍ ያለ መሆኑን አስምረውበታል። እግረ መንገዳቸውንም የህብረት ግንባሩን እንቅስቃሴ በማገዝ አላማውን ከግብ እንዲያደርስ ሁሉም ወገን ትብብሩን እንዲያደርግ ብሄራዊ ጥሪ አቅርበዋል። አቶ መርሻ ማብራሪያቸውን በዚህ በመቋጨት ወደ ቀጣዩና የስብስባውን ሰፊ ግዜ ወደ ወሰደው የጥያቄ መድረክ በመሸጋገር ተሳትፊዎች ያላቸውን ጥያቄ እንዲያቀርቡ ጋብዘዋል።

በስብሰባው ላይ በርካታ ጥያቄዎች ቀርበው ተገቢው ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። በተለይ የኢሕኣፓን ቀደምት የትግል እንቅስቃሴ በተመለከተ ለረዥም አመታት ሲጠቀሱ የቆዩ፥ በድርጅቱ ተፈጽመዋል የሚባሉ ስህተቶችና ጥፋቶች በተመለከተ ለአቶ መርሻ ከተሰነዘሩት ጥያቄዎች መካከል

 1ኛ ኢሕኣፓ ከጀበሃ ጦር ጋር ወግኖ የኢትዮጵያን ሰራዊት መውጋቱ እውነት አይደለምን ከሆነስ ለምን

 2ኛ በተመሳሳይ ከሱማሌ ጦር ጋር ሆኖ የኢትዮጵያን ጦር ወግቷል ይባላል ይህስ ለምን ሆነ

 3ኛ ኢሕኣፓ በደርግ ለተረሸኑት አባሎቹ ሕይወት መጥፋት ተጠያቂ አይደለምን

የሚሉት ግንባር ቀደሞቹ ጥያቄዎች ሲሆኑ በቅደም ተከተላቸውም መሰረት አቶ መርሻ መልስ ሰጠዋል።

  የመጀመሪያውን ጥያቄ በተመለከተ ሁኔታው ተፈጸመ በተባለበት ጦር ሜዳ የነበሩ የቀድሞ የኢሕኣፓ ሰራዊት አባላት በጋጣሚ በስብሳባው አዳራሽ እንደሚገኙ በማስታወስ ከሳቸው የተሻለ ምላሽ ሊሰጡበት እንደሚችሉ በመግለጽ አቶ መርሻ ተሳትፊዎችን ጋብዘዋል። በሜዳው የነበረው የቀድሞ ሰራዊት አባል ሲመልስ እንኳን ከጀብሃ ወግነን ልንዋጋ ቀርቶ ጠመንጃ እንክዋን ያልነበረን ተጠቂዎች ነበርን ሲል አስረድቷል። አቶ መርሻም አክለው ደርግ ለ17 አመታት ያሰራጨው ጸረ ኢሕኣፓ ፕሮፓጋንዳኘ በመደጋገም ሲሰማ እውነት ሊመስል መቻሉ እንጂ ኢሕኣፓ ከሱማሌም ሆነ ከጀብሃ ወግኖ ወገኑን አልወጋም ብለውል።

በመቀጠልም ደርግ የገደላቸው አባሎቻችን በማጣታችን ከማንም በላይ የተጎዳው ድርጅቱ ነው። ገዳዩ ደርግ እያለ ኢሕኣፓን ወንጀለኛ አድርጎ ማስቀመጡ ምን አይነት አመለካከትና ፍትህ እንደሆነ አይገባኝም። ካሉ በኋላ ኢሕኣፓ ስህተት አልሰራም አላልንም። ስህተት ተሰርቷል። ለደርግ ቀይ ሽብር ምላሽ በመስጠት የጀመርነው የከተማው የትጥቅ ትግል ተንዛዝቶና ከቁጥጥር ውጭ እስኪሆን መቀጠሉ ስህተት ነበር። በከተማ የትጥቅ ትግል መጀመራችን ግን አሁንም ቢሆን ስህተት አይደለም። በመጠኑም ቢሆን እራሱን ለመከላከል የማይሞክር ድርጅት ድርጅት አይደለም። ኢሕኣፓ እርምጃ የሚወስደው ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎችን ከሰጠ በኋላ ነው። ከተግባራቸው እንዲቆጠቡ ጠይቀን። አሻፈረን ብለው ሊያጠፉን ሲፈልጉ የግድ እራሳችንን መከላከል ነበረብን። ስህተቱ መንዛዛቱ ነው። ይህንንም ስህተታችንን በቀጣይ ባደረግነው ስብሰባ አምነን ይቅርታ የጠየቅንበት ነው። ኢሃፓ ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ይልቅ ስህተቱን ቀድሞ አምኖ ቀድሞ የሚያርም ድርጅት መሆኑን ያረጋገጥንበት ሁኔታ ነው። በማለት አስረድተዋል።

ሌላው ጥያቄ ከ ኦነግ ጋር አብረንኘ እንሰራልን ብላችኋል ታዲያ ኦነግ የመገንጠል አላማ ያለው ድርጅት መሆኑ ይታወቃልና ወያኔ ለሻቢያ ኤርትራንኘ እንደሰጠው እናተም ለኦነግ _ _ _ ልትሰጡ ነው ወይስ ህብረቱ በኋላ እንደገና ልትዋጉ። የሚል ነበር

እኛ ከየተኛው ተቃዋሚ ድርጅት ጋር ግንባር ፈጥረን እንሰራለን እያልን ያለነው ከሁሉም በፊት ቅድሚያ የሚሰጠው በመቻቻል በመግባባት ሃገራችን አሁን ካለችበት ችግር ማውጣቱ መሆኑን ስለምናምን ነው። ኦነግም ሆነ ሌላው ተቃዋሚ ድርጅት ኢትዮጵያዊ እስከሆነ ድረስ አብረን እንሰራለን በመቻቻል ውጠት እንደሚገኝምኘ እናምናለን።የሚል መልዕክት ያዘለ መልስ ሰጠተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ጥቂት የማይባሉ የስብሰባው ተሳታፊዎች በየተራ እየተነሱ በእለቱ ስብሰባ መርካታቸውንና እንዲህ አይነቱ ነገር መቀጠል ያለበት መሆኑን በመግለጽ ለእንግዳው ያላቸውን አክብሮትና ለድርጅቱም ያላቸውን ድጋፍ አንጸባርቀዋል። በእግጥም ስብሰባው መልካም መንፈስ የተላበሰና በኢትዮጵያዊው ወገን ሁሉ እየተለመደ የመጣው በልዩነት ላይና በስህተት ላይ የማተኮር ደካማ ባሕሪ ያልታየበት በመሆኑ እንደ አጀማመሩ ሁሉ በመልክም መንፈስ ተጠናቋል። የዚህ ስብሰባ ቀጣይ በመጪው እሁድ እንደሚደርግም ታውቋል።