Articles                                                 መጣጥፍ

  Back Home      Articles          Poems           News              Jokes               Email Us

        THIS WEBSITE IS CURRENTLY BLOCKED IN ETHIOPIA

 

በጀርመን ዘረኞች
የተደበደበው
ኢትዮጵያዊና ምርመራው

 

በዚህ በጀርመን በፖትስዳም ከተማ ከሣምንት በፊት በዘረኞች ተደብድቦ ክፉኛ የተጎዳው ኢትዮጵያዊ የጀርመን ዜጋ የጤንነት ሁኔታ አሳሳቢ ሆኖ እንደቀጠለ ነው። በትናንትናው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት ተጠርጣሪዎች ከተያዙ ወዲህ የጀርመን ፌደራላዊ አቃቤ-ሕግና ፖሊስ በተለይ ከዓይን ምስክሮች የተገኙ መረጃዎችን መመርመር ቀጥለዋል። በሌላ በኩል ትናንት ተይዘው የታሰሩት ሁለት ተጠርጣሪዎች የ 37 ዓመቱን ጎልማሣ ኢትዮጵያዊ አልደበደብንም ሲሉ ክሱን በማስተባበል ላይ ናቸው። ሃኪሞች እንደሚሉት የቀኝ አክራሪዎች የጥቃት ሰለባ የሆነው የሁለት ልጆች አባት አሁንም ለሕይወቱ አደገኛ በሆነ ሁኔታ ላይ ነው። በበርሊን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ምዕመናንና አገልጋዮች ትናንት ድርጊቱ በተፈጸመበት ቦታ ተገኝተው በጸና የተጎዳው የአገር ተወላጅ ምሕረት ይወርድለት ዘንድ ጸልየዋል። የደብሩ አለቃ አባ ገሪማ ተሥፋዬ ሕመምተኛውን ሊጠይቁ ሞከራቸው አልተሳካላቸውም።  የበርሊኗ ቤተ-ክርስቲያን አክራሪውን ዘመቻም አጥብቃ ተቃውማለች። ይህ በዚህ እንዳለ ትናንት ማምሻውን ሺህ ገደማ የሚጠጉ ሰዎች ፖትስዳም ውስጥ አደባባይ በመውጣት የዘር ጥላቻን ኮንነዋል።