Articles                                                 መጣጥፍ

  Back Home      Articles          Poems           News              Jokes               Email Us

        THIS WEBSITE IS CURRENTLY BLOCKED IN ETHIOPIA

የአዛውንቱ ብሶት

 ረሃብ የለውጥ ዋዜማ ምልክትነቱን ዳግም እውን ?
 

አንድ ሕዝብ ታስተዳድረኛለህ ብሎ የመረጠውን መንግስት ማንነትና ምንነት በብዕሩ ም ሆነ በአንደበቱ ለመግለጽ ይፋ መብት ሊኖረው እንደሚገባ ግልጽ ነው። ይህን ሃቅ የሰለጠኑት ሃገሮችም ሆኑ የ3ኛ አለም ሃገሮች መንግስታት አሌ አይሉት ም። ጥያቄው ያለው በ3ኛው አለም በተለይም በአፍሪካ የሚገኙ ሃገሮች ሕዝብ የሚ ያስተ ዳድረውን መንግስት የመምረጥ እድል አለው ወይ ? የሚለው ነጥብ ላይ ይ መስለኛል።መልሱ ደግሞ የለም ነው። በአፍሪካ ሃገሮች መንግስታት የሚያስተዳድሩትን ህዝብ ይመርጣሉ እንጂ ህዝብ የሚያስተዳድረውን መንግስት ሲመርጥ አልታየም። IMF ን ላለማስቀየም ለይስሙላ የሚደረጉትን የምርጫ ድራማዎች እንዳሉ አልቆጥራ ቸውም።

 የሚያስተዳድረውን መንግስት የመምረጥ መብት የተነፈገ ህዝብ ደግሞ ያልመረጠ ውን መንግስት ማንነትና ምንነት በይፋ የመግለጽ መብት ይኖረዋል ብሎ መጠበቅ የአህያና የጅብን ፍቅር አይነት ተረት፤ ተርት ነው። አንድ ሃቅ ግን አለ። የአንድ መንግስት ማንነት በሚያስተዳድረው ሕዝብ የማሕበራዊ ሕይወት እድገትና ውድቀት ይለካል የሚል። ትክክል።

" ደስተኛ ህጻናት የሡለጠነ ህብረተሰብ ምልክቶች ናቸው" ከሚለው ጥቅስ ጋር ተዛ ማጅ የሆነ ሃቅ ነው። ደስተኛ ሕዝብም የጠንካራ መንግስታት መገለጫ ነው። በተቃ ራኒው ደግሞ ረሃብተኛና ችግርተኛ ህዝብ የመሰሪ፤ የጀብደኛ፤ የሙሰኛ፤ _ _ _ _ _ መንግስታት ምልክቶች ናቸው።

የረሃብ መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል። የተፈጥሮ ሚዛናዊነት ሲጓደል ረሃብ ሊከሰት ይችላል።ሌላም ሌላም _ _ _ እየባሰ ያለው ግን የፍጡር ሚዛናዊ አሡራር በመጓደሉ የሚከሰተው ረሃብ ነው። የጽሁፌ አቅጣጫ ወዴ ት እያመራ እንደሆነ የርሃብ ሙሾ ማውረድ እጣ ፈንታው ለሆነው ለኢትዮጵያዊው ወገን የሚጠፋው አይደለም።

መንግስታችንኘ ከ14 ሚልዮን ህዝብ በላይ ለርሃብ እንዲጋለጥ በቀጥታም ሆነ በተዘ ዋዋሪ ምክንያት የሆኑ እኩይ ተግባራትን ፈጽሟል። ይህንን ሃቅ ወደ ጎን ትተው፥ ለረሃብተኛው ወገን እርዳታ እንዲደርስ የልመና እጆቻችንን የዘረጋነው እንደ አለፉት መንግስታት ዘግይተን አይደለም የሚል ዲስኩር ያሰሙናል። ረሃቡን አልደበቅንም ይሉ ናል። ያለፉት መንግስታት የሰሩትን ሠህተት አልሰራንም ይሉናል። የረሃብተኛው ህ ዝብ ቁጥር ደግሞ ባለፉት ሁለት መንግስታት ለርሃብ ከተጋለጠው ሕዝብ ጠቅላላ ድምር በልጦ መገኘቱ ግን ከስህተት አልጣፉትም።

በአለፉት ቅርብ አመታት ኢትዮጵያ ተረፈ ምርቷን ለደቡብ አፍሪካ ኤክስፖርት አድ ርጋ እስከ መሸጥ ያደረሳት የኢኮኖሚ እድገት ላይ መገኘቷን ጠቅላይ ሚንስትራችን ሲገልጹልን እሰይ እሰይ ብለናል። ዛሬ ደግም የሕዝባቸው ሲሶው የሚላስ የሚቀመስ ማጣቱን በዛው አንደበት ሲናገሩት ትናትን ያስታወሰ ሁሉ ግራ ገብቶታል። ተረፈ ምፍርት ከመሸጥ እሰከ ረሃብተኝነት ያለውን ረዥም የውድቀት ቁልቁለት ለመውረ ድ የፈጀባቸው ግዜ በጣም አጭር መሆኑ ብዝዎችን አነጋግሯል።

ይህው ጉዳይ እኔንም አስገርሞኝ አንድ በቅርቡ ከአገርቤት ልጃቸውን ሊጠይቁ ወደ ባህር ማዶ ለመጡ አባት ጥያቄዬን አቅርቤላቸው ነበር። ታዲያ የሰጡኝ መልስ ሳል ወድ በግዴ እንድስቅ አድርጎኛል። እስኪ ካዛውንቱ ጋር ያደረኩትን ውይይት ተከታ ተሉት፥

ለመሆኑ አልክዋቸው፥ ለመሆኑ በኢትዮጵያ መንግስት ከቅርብ አመታት በፊት ከበቂ በላይ አምርተን ለደቡብ አፍሪካ እስከመሸጥ ደርሰናል ተብሎ የተወራው ውሸት ነው ማለት ነው ?

" ልጄ ነጋዴ ትርፍ ካገኘበት ደቡብ ፥ ሰሜን፥ ውጭ፥ ውስጥ ብሎ አቅጣጫ አይ መርጥም የሚያዋጣውን ነገር አፈር አይል አተር መሸጥ ሠራው መሆኑን እያወቅክ ምን አጠራጠርሃ ?" በማለት ጥያቄዬ በጥያቄ መለሱልኝ

አባባሌ ትናት ከፍጆታው በላይ ማምረት ችሎ የሸጠ ህዝብ ዛሬ ለረሃብ መጋለጡ _ __ _ ብዬ ሳልጨርስ አቋረጡኝና

" ልጄ ተርፎኝ ሸጥኩ ያለው መንግስት እንጅ ሕዝብ አይደለም እኮ" ብለው ሳቅ ሲሉ የፈገግታቸው ምስጥር ባይገባኝም አብሬ ፈገግ በማለት ሌላ ጥያቄ በማስከተል

ህዝብ ያላመረተውን መንግስት ከየት አምጥቶ ይሸጣል ብለው ነው? አልኩ

አዛውንቱም ከበፊቱ በበለጠ ሳቅ ብለው

"አሁንስ ቢሆን ሕዝቡ የሚላስ የሚቀመስ ባጣበት ሳአት መንግስት ገንዘብ ካገኘን እ ህሉ ገበያ ላይ ስላለ ገዝተን ለረሃብተኛው ማቅረብ እንችላለን አይደል እንዴ ያለ ው? ታዲያ ህዝቡ ያላመረተውን መንግስት ከየት አምጥቼ እሸጣለሁ ብሎ ይመስል ሃል? አየህ ልጄ ነጋዴ ገንዘብ ካገኘበት ከማንም ገዝቶ ለማንም ለመሸጥ ምርጫ አ ያደርግም። ነጻ ገባያ ተብሎ የለ፥ ከየትም ገዝቶ ጥሩ ዋጋ የሚከፍለውን አወዳድሮ መሸጥ የነጋዴው መብት ነው።አቅም አጥቶ መግዛት ላልቻለውም ሸማች የመራብ መ ብቱ ተጠብቆለታል።የኢትዮጵያ መንግስትም ያደረገው ይህንኑ ነው።ጥሩ ዋጋ መክፈል ለቻለው ለደቡብ አፍሪካ መንግስት ሸጠለት አቅም አጥቶ መግዛት ላልቻለው ለኢት ዮጵያ ገበሬ ደግሞ የርሃብ መብቱን ጠበቀለት።ነጻ ገበያ መባሉ ለዚሁ አይደል? በረሃብተኛው የሞት አፋፍ የጠኔ ጣርና ሲቃ ኪሳቸውን ሊያደልቡ እየቋመጡ ያሉት ወገኖች ሳስተውል፥ ሃብት የሚገኘው አንድም ሃገር ስትለማ አንድም ሃገር ስትጠፋ ነው በማለት አንድ ታዋቂ ደራሲ ዋና ገጸባህሪውን ተጠቅሞ ያስተላለፈው መልዕክት ዕውነትነቱ ይገዝፍብኛል።"በማለት ንግግራቸውን ሲገቱ ሞኝ ሁለቴ ይስቃል፥ አንዴ ም ሳይገባው አንዴም ሲገባው እንዲሉ እኔም የአዛውንቱ አነጋገር ለመጀመሪያ ግዜ ግልጽ ሆኖልኝ ከልቤ ሳቅኩ።

ያነጋገራቸው ላዛና ውስጠት ስላስደነቀኝ አዛውንቱ ቶሎ እንዳይለዩኝ ፈልጌ ወዲያ ውኑ ሌላ ጥያቄ አስከተልኩ።ለመሆኑ የርሃቡ ምክንያት ምንድነው ተባለ አልኳቸው?

"አይ ልጄ እስኪ የረሃቡን ምክንያት ከመገምገም ለረሃብተኛው ዳቦ ማቅረቡ ይቅደ ም።አንዱም ሡራተኛውን ህዝብ በጥብጦ ለችግርና ለስራፈትነት የዳረገው ይሄ ግምገ ማ ያሚሉት ነገር ነው። ግምገማውን ራሱን ነው መገምገም።" በማለት ባላሰብኩት መንገድ የመለሱ መልስ አሁን ለፈገግታ አቀበለኝ።እኔም የአዛውንተኑ ትክክለኛ አባ ባል በመደገፍ፥

እሱማ ልክ ብለዋል ረሃብተኛውን ማትረፍ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑ አያጠ ያይቅም ለዚህም ነው በአሁኑ ወቅት በውጭው አለም የሚገኝው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ ረሃብተኛ ወገኑን በመርዳት የዜግነት ግዴታውን ለመወጣት እየተረባረበ የሚገኘ ው አልኩ።

"ማለፊያ ልጄ ማለፊያ አድርጋችኋል ወገን ከመቼውም ግዜ በበለጠ በወገን ላይ ተስፋውን የጣለበት ግዜ ነው። ሕይወትን ያህል ውድ ነገር የማቆየት ተስፋው በናተው ላይ ነው። ሌላ ሌላውን ተወው ብለው ተከዝ" አሉ።እኔም ቀጠል አድርጌ ታዲያ የዚህ ሁሉ ችግር መጨረሻው መቼና እንዴት ይመስልዎታል አልኳቸው?

አሁንም ከትካዜያቸው ነቃ እንደማለት ብለው "አንዱም ትልቁ ችግራችን የቅርብም የሩቅም ራዕይ ማጣታችን ነው። ራዕይ ከማጣት ደግሞ ሩህን ማጣት ይሻላል።እየሞቱ መኖር ያሰቃያል ሞት ግን ይገላግላል ። ሃገራችንም ራዕይ ያለው ተቆርቋሪ አጣች ህብረትና መቻቻል አልሆንልን አለን።"  በማለት አሁንም ተከዝ ሲሉ እኔም ቀጠል አድርጌ

ሊነጋ ሲል ይጨልማል እንዲሉ ረሃቡ የለውጥ ዋዜማ ምልክትነቱን ዳግም እውነት ቢሆንስ ይህ ከራዕይ አይመደብም አልኳቸው?

"እውነት ከሆነማ ከራዕይም በላይ እንጂ የሚመደበው።" በማለት የጥያቄዬ ስህተት አርመው ንግግራቸውን ቀጠሉ። "እናም የተስፋችን እውነት የመሆን ተስፋ ምን ያህል ነው? የሚለው ነጥብ ነው ዳገቱ። አባባልህ እንደገባኝ ከሆነ በንጉሱ ዘመን መጨረሻ ላይ የተከሰተው ረሃብ ለለውጥ ምክንያት እንደሆነ ሁሉ ዛሬም ታሪክ ራሱን ቢደግምስ የሚል ነው። ታሪክ ራሱን ደግሞ ካየን እሰየው ነው። ረሃቡ ለለውጥ ምክንያት እንዲሆን ግን አጋዥ እንቅስቃሴዎች ያስፈልጉታል። አጋዥ እንቅስቃሴዎች ሳይኖሩ ታሪክ ራሱን መደገም ስላለበት ብቻ ረሃቡ በአንድ ጀንበር ለውጥን ጸንሶ ይገላገለዋል ብሎ ማሰብም ባዶነት ይመስላል። በርግጥ የለውጥ ጽንስ ከግፍ ነውና የሚያዝ ያሳለፍነው ግፍ ብዛት ደግሞ ለተጸነሰው የለውጥ ሽል እድ ገት በቂ በመሆኑ ረሃቡ ደግሞ ምጡን ቢያፋፍመው ተስፋችንን የመታደጋችን ተስፋ ባዶ ነው አልልም። ግን እንነጋገር፤ እንቻቻልና ያማይቻለውን እንዲቻል እናድርግ። አልያ _ _ _ _ _ _ _ _ ተግባር ያልደገፈው ራዕይ _ _ _ _ራዕይ አይሆንም _ _ _ _አሉና ንግግራቸውን ገቱ

አዛውንቱ ያጭወተኙ በህዝባችን ላይ ለረዥም ግዜ ሲፈጸምበት የቆየው ግፍና ዘረፋ ሳያንስ ይባስ ብሎ ለርሃብ እንዲጋለጥ መደረጉ እያንገበገባቸውና ከሁሉም በላይ ደግ ሞ የዚህ ግፍ ችግር መጨርሻው መቼ እንደሆነ የሩቅም የቅርብም ራዕይ መጥፋቱ እያሳዘናቸው ነው።

እኔም ሆንኩ ሌላው ኢትዮጵያዊ ቁጭታችንና ንዴታችን ከአዛውንቱ የተለየ የሚሆን አይመስለኝም።ታዲይ እንደ ቁጭታችን ሁሉ እኛም አንድ ሆነን ተቻችለን ተስማምተን መስራት ያለብን ግዜ አሁን ነው።የስካሁኑ ልዩነትና መቃቃር እንዳልኖርንበት ዘመን ቆጥረን፥ የውሾን ነገር ያነሳ _ _ _ ይሁን ብለን በአዲስ መንፈስ እንነሳ። ረሃብተኛ ውን ወገን ከሞት አፋፍ እናድን። በማለት የዛሬው ጽሁፌን በዚሁ እቋጫለሁ።

  ሰላም ለሚፈልጋት ለኢትዮጵያ ህዝብ ትሁን

                                    ሳ/አ