"በአንጻራዊነት...."
የመሪዎች ማጭበርበሪያ ቁል ቃል
|
በአንጻራዊነት ሲታይ ከፊውዳሉ ሠርኣት በተሻለ ዛሬ ህዝቡ የሃብቱም የመብቱም ተጠቃሚ ሆኗል። ኮለኔል መንግሥቱ አዲሶች በመሆናችን የፕሬስ መብትንና ህጉንም በማስፈጸም አኳያ ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ ይሁንና ካለፈው ሠርኣት ጋር በአንጻርዊነት መታየት ያለብት ጉዳይ ነው። መለስ ዜናዊ ህዝብ ደግሞ በአንጻራዊነት ከኢሃዴግ ይልቅ ደርግን ከደርግ ይልቅ ንጉሡን ይመርጣል ታዲያስ ጎበዝ ወያኔን የሚያስመርጥ የነገው ምን ይሆን አያስብልም። ከቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንትና የ 27 አመቱ የአርነት ተጋይ ኒልሰን ማንዴላና ከጁሌስ ኔሬሬ በስተቀር ሠልጣኑን በሰላም ለቆ ወይም ለተተኪ አሳልፎ የሰጠ የአፍሪካ አገሮች መሪ አልታየም ። ለምን ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት መሞከር የአንባቢን ግንዛቤ ማሳነስ ይሆናል። የአፍሪካ ሃገሮች የመንግስት ሹም ሽር የሚደረገው በህዝቡ ምርጫና ፍላጎት ወይም በሁለትና ከዚያም በላይ በሆኑ የፖለቲካም ሆኑ የጦር ሃይሎች ነጻ የመሳ ለመሳ ትግልም ሆኖ አያውቅም። 3ኛው እጅ በመሆን የሠልጣን ማረካከቡ ሃላፊነት ያለምንም ድካምና መሰልቸት የሚፈጽሙልን አሜሪካኖች ለመሆናቸው ከኛው አምባሳደር ከኸርማንኮል የ 1983 አ _ ም እንቅስቃሴ ማስታወሱ= በቂ ነው። የሚገርመው አሜሪካኖች ይህ ተግባራቸው በውለታ መዝገብ እንደተጻፈላቸው ማሰባቸው ነው።ለማጣቀሻነት አነሳሁት እንጂ የዛሬው ነጥቤ ይህ አይደለም። የዛሬው የጽሁፌ አቅጣጫ አንጻራዊነት በሚለው ቃል ዙሪያና በትርጉሙ አተገባበር ላይ የኢትዮጵያ መንግስታቶች ያዳበሩትን የወልና ኢ ፍትሃዊ የሆነ አሡራር በመቃኜት ከሌሎች መሪዎች ምን መማር አለባቸው ወይም ነበረባቸው የሚሉትን ጉዳዮች ለመዳሰስ ነው። አንጻራዊ የሚለው ቃል ማነጻጸር ከሚለው ግሠ የሚወለድ ሲሆን ተዛማጅ ትርጉሙ ማወዳደር ፤ ማስተያየት ፤ ማመዛዘን ፤ ወይም ሚዛናዊ በሆነ መልክ መመልከት የሚሉት ናቸው። ቁልፍ ትርጉሙም ፍትሃዊ የሚለውን ክቡር ቃል ያዝላል። የኢትዮጵያ መንግስታት ስንል ለግዜው እንደ አብነት የምንወስዳቸው የደርግን ሠርአትና ወቅታዊውን የኢሃዴግ መንግስት ይሆናል። በኮለኔል መንግስቱና በአቶ መለስ የሚመራው የኢትዮጵያ የልዩ ልዩ ጊዜ መንግስታት የወል የሆነው ዋንኛው ባህሪያቸው ኢ ፍትሃዊነት ኢ ዲሞክራሲያዊነትና አምባገነንነት ነው። ኮለነል መንግስቱ ሶሻሊዝምን አውጀው በፊውዳሊዝም መቃብር ላይ አዲሲቷን ኢትዮጵያ ሊገነቡልን ኢምፔርያሊዝምን እንደ እንቧይ ሊያፈርጡልን ቃል የገቡት ቀይ ቀለም ይሁን ደም ባላውቅም (ግዜው ደም ከቀለም የርከሰበት ስለነበር ማለቴ ነው) የተሞላ ጠርሙስ በመከስከስ ነበር። ማንኛውም አመለካከትና እምነት ትክክልኝነቱ ወይም ስህተቱ ሊገመገም የሚገባው በዛው በወቅቱና በወቅቱ ብቻ እንዴኒ በታሪክዳነት ከተመዘገበ በኋላ አለመሆነን ስለምዳዳማ የኮለነኔል መንግስቱን የሶሻሊዝም አዋጅ ስህተትነት ለማውሳት አይደለም አነሳሴ። የኔ ትኩረት ኮለኔሉ በሶሻሊዝም ቁልቁለት ላይ ሲንደረደሩ ከኋላቸው የነበረውን የንጉሳዊ አገዛዝ በደልና ሃጢያት እያጋነኑ በመውቅስ በተጓዳኝም በሳሣቸው የሚመራውን መንግሠት ለሕዝብ አሳቢነት እየዳሰኮሩ እንደነበር ለማስታወስ ነው ።አሁንም የንጉሣዊው ሠርኣት አላጠፋም አይደልም ነጥቤ። የኛ መዳሪዎች አንጻራዊ አመለካከታቸው ጭፍን ያለና አ ^ፍትሃዊ እየሆነ መሄድ መለመዱን ላስታውስ ፈልጌ ነው። መጀመሪያ ያለፈውን በትጋት መውቀስ አስከትሎም ቁንጽል ለውጦችን እንደ አብነት በመጥቀስ በተጋነነ አንጻራዊ አመለካከት እራስን ማሞገስ የአቶ መለስም የኮለኔሉም የጋራ ባህሪ ነበርም ነውም። ደርግ የመሣፍንት አገዛዝ እንዲህ ፈጥሮ _ _ _ የጉልተኛው ሠርኣት _ _ _ ይህን አድርጎ ፊውዳሊዝም _ _ _ ምን ቅጡ _ _ _ በማለት የወደቀና ያለቀለትን ሠርኣት በመኮነን ያባከነው ጊዜና ሠልጣኑን ለማመቻቸት ያወጣው አላስፈላጊ ወጪ ያጠፋው ህይወት ሲታሰብ ይዘገንናል። የትናትን ስህተት በመኮነን እንጂ በማረሙ ተግባር ላይ የተሳተፈ መንግስት አላየንም።ለዚህም ይመስለኛል አዲስ መጭው መንግስት አሮጌውን ሲወቅስ ሕዝቡ ደግሞ ሂያጁን ሰያመሰግን መጪውን ሲኮንን የሚኖረው። የወደቀን መንግስት ስህተት አብዝቶ ማውራቱ ጠቃሚነት እንደሌለው ይቅር ብቀላ ካሉት ከ ማንዴላ መማር የቻሉ አይመስልም። እንደኔ እምነት አንድ መንግስት 95 ፕርሰንት አጥፊ ሆኖ 5 ፐርሰንትም ብትሆን ጥሩ ሠራ ካለቺው እንደ አብነት መጠቀስ አለበት ባይ ነኝ። ደርግን በቀይ ሽብር እንደምናስታውሰው ለመሰረተ ትምህርት መስፋፋት ባደረገው ጥረትም ልናስታውሰው ይገባል ባይ ነኝ።አንጻራዊ አመለካከት ፍትሃዊ የሚሆነው በዚህ መልኩ ብቻ ይመስለኛል። ኮለኔል መንግስቱ ግን ይህንን ለማድረግ አልፈቀዱም። በሰፈሩት ቁና ሆነና አቶ መለስማ ጭራሹኑም እሳቸው ካድሬዎቻቸው አንጻራዊ የሚለውን ቃል የፖለቲካው ወለምታ መታሻ አድርገውታል። የነጻ ጋዜጣ አዘጋጆችን ሸበብ ያደርጉና ምነው ሲባሉ ካለፈው ሠርኣት ጋር አንጻራዊ አድርገን ልንመለከተው ይገባል። በደርግ ሠርኣት ___ _ _ _ _ አልነበረም ዛሬ _ _ _ _ አለ።በማለት ይቆጡናል። 5 ብር የሚከራየውን ቤት 100 ብር አድርገው ደሃው እንዴት ልክፈል ሲል ነጻ ገበያ ብለናል አንተም በነጻ ገበያው ተወዳደር።ይሉታል። 5 ብር የሌለውን ሰው በነሳው ገበያ ተወዳደር ብሎ ሹፈት።አንጻራዊነት በወያኔ አገላለጽ ከደርግ ጥፋት ተቀድቶ የወያኔን ጉድለት መሙያ መሆኑ ነው። እኔ የምለው ደግሞ አንባቢዬን ማስጎምጀት አይሁንብኝና ነገ የአቶ መለስ መንግስትም ቢወርድ የሰራት ኢምንት ጥሩ ሠራ ካለች ሊመሰገንበት ለጥፋቱም ሊጠየቅበት ይገባል ባይ ነኝ። በትክክል ሲታይ የፕሬስ ነጻነት የሰጠን ኢሃድግ አይደለም ። የአለም ወቅታዊና ተጨባጭ ሁኔታ አስገዳጂነት እንጂ ። ኢሃድግማ በህገመንግስቱ የወንጀለኛ መቅጫ ሊጠቃለል የሚገባውን የፕሬስ ነጻነት እራሱን የቻለ ህግ ቅርጾለት አጠበበው።ዛሬ የሚነግሩን ካጫካ ይዘውልን የመጡት ገጸበረከት እንደሆነ አድርገው ነው።ዋናውን ነጥቤን ላለመልቀቅ እንጂ ብዙ ማለት በተቻለ ነበር። የኛም ሆኑ ሌሎች የአፍሪካ መሪዎች አንድ ሊያውቁት የሚገባ ነገር አለ። ይህም የህዝብን መብት በማስጠበቅና በመጠበቅ የሚሞቱለትን ወንበራቸውን ማጥበቅ እንደሚችሉ ነው ።የሚያደርጉት ግን ተቃራኒውን ነው። ለሠልጣን ያላቸው ፍቅር አውሮአቸው በገናለገና ሠጋት የህዝብን መብት ይገፋሉ ።ይህንኑ ሠህተታችውን ለመንገር የደፈረውን ያጠፋሉ ። ይህ በቀጠለ ቁጥር በውጥረት ላይ ውጥረት እየጨመሩ እምነታቸውን በህዝ ላይ ሳይሆን በሚቀልቧቸው ጥቂት አጃቢኦቻቸ ላይ ሊጥል ይገደዳሉ ።አጃቢውም የህዝብ ልጅ ነውና ፊቱን ያዞረ ቀን _ _ _ ያዘዙበት ሃገር ጥርኝ አፈር ለመቀበሪያቸው እንኳ አያገኙትም። ለዛውም እድል ብሎ ካመለጡ ማለቴ ነው።አልያም በእሠር መማቀቅ ነው። አንድ ጸሃፊ ስለ ፕሬስ ነጻነት ሲገለጽ የጠቀሳትን ነገር እዝህ ላይ ማንሳቱ ተገቢ ይመስለኛል። የፕሬስ ነጻነትን ለህዝብ ከሚሰጠው ጠቀሜታ የበለጠ ለመንግስት የሚስጠው ጠቀሜታ ይበልጣል ይልና። ሲያስረዳ ህዝብ የሚለው ቃል አብስትራክት ነው ያም ማለት ግኡዝ ያልሆነ ማለት ነው። ህዝብ ወጥ የሆነ ሃሳብና አመለካከት የለውምም ሊኖረውም አይችልም። ሃሳቦች በግለሰቦች መንጭተው በስፋት ተንሸራሽረውና ዳብረው የብዙሃኑን አዎንታ ሲጎናጸፉ እንደ ህዝብ ሃሳብ ብቅ ይላሉ።መንግስት ማለት ደግሞ ግኡዝ አንድ ወጥ በሆነ መመሪያ የሚንቀሳቀስ በመሆኑ ህዝብ ከሚለው አብስትራክት አካል በፈጠነና በተቀናጀ መልኩ ሊንቀሳቀስ ይችላል ማለት ነው። በመሆኑም አንድ መንግስት ህዝቡ የመናገር መብቱን ተጠቅሞ የሚያንሸራሽራቸውን ሃሳቦችና አስተያየቶች በመጠቀም አካሄዱን ሊያስተካክል ትልቅ እድል ይሰጠዋል። ይህን ያላደረገ መንግስት ደግሞ በቀላሉ ሊፈታ የሚችለውን ይህዝቡን ችግር ወድ በማፈን ወደ ውጥረት ብኋላም ወደፍንዳታ ይያደርስን የአሱን መጥፊያ ያዘጋጃል።ይላል። ለዝህ አባባል ዋቢ የእሆነው የደርግ መንግስት ህዝብን አፍ አዘግቶ በመቀመጡ በየወቅቱ እየሻከረ የመጣውን የህዝቡን ሠነ ልቦናዊ ይዘት ለመረዳት እንኳ ሳይችል በመቅረቱ በርካታ ማስተካከልና ማለፍ የሚችላቸው ሠህተቶቹ ተደማምረው ለውድቀት ዳርገውታል።የጎንደር ህዝብ ላይ ግፍ የፈጸመውን መላኩ ተፈራን እንኳ በጎንደር ሕዝብ ጥያቄ መሰረት ለፍርድ ቢያቀርብ ዛሬ የኢሃድግን ሡራዊት የጀርባ አጥንት ሆኖ ለሠልጣን ያበቃው የጎንደር ወጣትን ለጦርነት ባላነሳሳ ነበር። ወያነ ደግሞ ሕዝብ እንዳይታፈን አፉን ለቆ እንዳይተነፍስ ጉሮሮውን አንቆ ጥቂት ቢሆን ከደርግ ሠህተት የተማረ ይመስላል። አቶ መለስም ኮለኔል መንግስቱም ከነጁሌስ ኔሬሬና ማንዴላ ያልተማሩት ነገር ህዝብን በማክበር መከበር እንደሚቻልና ህዝብን የመናቅ መጨረሻው ውድቀት መሆኑ ነው። ጁሌስ ኔሬሬ በገዛ ፈቃዳቸው ሠልጣን ሲለቁ ቤሳ ቤስቲን ያልነበራቸው በመሆኑ የጡረታ ግዚያቸውን በግብርና እንዲተዳደሩበት ትራክተር የሰጣቸው ህዝብ ነበር። ጽድቁ ቀርቶ በቅጡ በኮነነኝ እንዳለቺው ሴት እንዲህ አይነቱን ሠነ ምግባር እንኳን ባንጠብቅም ህዝብን የማክበሩን ባህሪ ቢያዳብሩልን እኛም መሪዎቻችንን ለመቅበር ሳይሆን ለመጦር በታደልን ነበር። እናም መንግስታቶቻችን አንጻራዊ የሚለውን ቃል የወለምታቸው ወጌሻ በማድረግ ከሚመጻደቁብን ወደኋላ ሄደሽ በሃሳብ ከማለም ቀኑ እንዳይመሽብሽ ትናት ዛሬ አይደለም እንዳለው አቀንቃኝ ዛሬ ላይ ቆመው ስለ ትናት ከሚነግሩን ስላለንበት ዛሬ ቢያወሩልን ሳይሆን ቢሡሩልን ከተቻለም ሠለነገ ቢያስቡም ሸጋ ነው እያልኩ ልሰናበት
|