Back Home               Articles              Poems           News              Jokes               Email Us

        THIS WEBSITE IS CURRENTLY BLOCKED IN ETHIOPIA

 

ባለስልጣኑና የታክሲው ሹፌር


 

አንዱ የወያኔ ባለሠልጣን ድንገት መኪናው ተበላሽቶበት ታክሲ መጠቀም ይገደድና አስቁሞ ይሳፈራል። በ6ኪሎ የሰማእታት ሃውልት ሠር እየተጠመዘዙ ሳለ ሃውልቱ ላይ ያሉት የሰማእታት ምስሎቹ ጥቂቶቹ አዲስ ቅብ ተቀብተው ቀሪዎቹ ደግሞ አለመቀባታቸውን ያስተዋለው ባለስልጣን ፥ ? .........! "

"ለምንድነው ጀምረው የሚተውት?" ከጀመሩ መጨረስ አልያም አለመ ጀመር ይሻላል በማለት አንገቱን አጠማዞ ሃውልቱን እየተመለከተ የወ ቀሳ አስተያየቱን ይሰጣል። ባለታክሲም ጨዋታኛ ቢጤ ኖሮ ሃውልቱን መልከት አድርጎ እንዲህ ይላል

" የተቀቡት በተሃድሶ ያመኑት የጠቅላይ ምኒስትሩ ደጋፊዎች ያልተቀ ቡት ደግሞ መበስበስን የመረጡት ውህዳኖቸ ወይም ሙሰኛ ሆነው የ ተገኙት የነሠዬ ደጋፊዎች ሳይሆኑ አይቀሩም" በማለት እራሱም ፈገግ እያለ ተሳፋሪውንም ሊያስቅ ሲሞክር ያላሰበው ነገር ተከተለ።

ባለስልጣኑ " አፍህ ዝጋና ሠራህን ሠራ ተሃድሶ ገለመሌ ውሻ ! "

ሹፌር "ምን ያሳድብሃል ካላሳቀህ አለመሳቅ እንጂ የምን ስድብ ነው?

ባለስልጣን " አተ አፍህ ዝጋ! ውሻ !......"

ሹፌር " አንተም አፍህን ዝጋ ! አትሳደብ"

ባለስልጣን " እዋ! አንተ ውሻ !.........ዛሬ "

ሹፌር " ውሻ አትበለኝ"

ባለስልጣን " እልሃለሁ ውሻ ! ውሻ ነህ ውሻ! ምናባክ ታመጣለህ?" ብሎ ሽጉጡን ከጎኑ ላጥ አድርጎ ይደግንበትና

ባለስልጣን " ውሻ እልሃለሁ ውሻ ነህ ምናባክ ታመጣለህ?"

ሹፌር " ምን አመጣለሁ አልኩኝ ውሻና ስው ለይ አልኩኝ እንጂ"

ባለስልጣኑም ሽጉጡን እንደደገነበት " ሰው አይደለህም እኔ ውሻ ብዬሃለሁ በቃ ምን ትሆናለህ?"

ሹፌር " የግልህን አመለካክት ማንጸባረቅ መብትህ ነው"

ባለስልጣን " አንተ ዝምበል እዋ!...... ውሻ ብዬሃለሁ ውሻ ነህ"

ብሎ በሽጉጡ አፈሙዝ ጉንጩን ወጋ ሲያደርገው ባለታክሲው በድንጋ ጤ መንዳት ስላስቸገረው መኪናውን ወደ መንገድ ዳር ወጣ አድርጎ አቆመ።

ባለስልጣኑም አላፊ አግዳሚው እንዳያይ ሰግቶ  " አታቁም ንዳ ንዳ ብያለሁ አንተ ውሻ ንዳ" እያለ ሽጉጡን ወደታች ዝቅ አድርጎ የሚመለከታቸው ሰው እንዳለ ለማረጋገጥ ዙሪያውን ገልመጥ ገልመጥ እያለ ሲመለካከትለት ፋታ ያገኘው ሹፌር  " የት ሃገር ነው ውሻ መኪና የሚነዳው " በማለት የመኪናውን በር ከፍቶ እግሬ አውጭኝ ብሎ በመፈርጠጥ ከአጣብቂኙ ተርፏል።