ፕሬዘዳታችንና ጠ/ሚንስትራችን
|
ፕሬዘዳታችን ህዝቡ ስለሳቸው ያለውን አመለካከትና አስተያየት ከተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች እየሰሙ ይበሳጫሉ።በተለይ ደግሞ በቀልድ መልክ የሚወራ ባቸውን ወሬ አቀባዮቻቸው ሲነግራቸው ንዴታቸው እየተባባሰ በመሄዱ ጉዳዩን ለጠቅላይ ሚንስራችን አሳውቀው መፍትሄ እንዲፈልግላቸው ለማድረግ ወስነውለጠቅላይ ሚንስራችን ያዋይዋቸዋል።ጠቅላይ ሚንስራችንም እንደተለመደው ለሕዝብ ያላቸውን ንቀት በማስቀደም ይሄ ደደብ ህዝብ ሰደበኝ ብለው ነው የሚበሳጩት የፈለገውን ቢናገር እርስዎ ለእንደዚህ አይነት ጉዳይ ጆሮ አይስጡ ዝም ብለው ሠራዎን ይስሩ። በማለት ለማረጋጋት ይሞክራሉ። ፕሬዘዳቱም ለጥቂት ግዜ ያህል እንደተባሉት ሁሉን ንቀው ለማለፍ ቢሞክሩም ቀልዱና ፉተታው እየጠነከር በመሄዱ አሁንም ወደ ጠቅላይ ሚንስራችን ሄደው አንድ መፍትሄ ካልሰጠህኝ ስልጣኔን እለቃለሁ በማለት ምርር ብለው ተናገሩ። ዘዴኛው ጠቅላይ ሚንስትርም ሰውን ለምን ቀለድክ ብለን ማሰርም መክሰስም አንችልም ቀልዶች ደግሞ ፈጣሪያቸው ስለማይታወቅ ማስረጃ አቅርቦ መክሰስ ስለሚያስቸግር ለምን ይህን ደደብ ሕዝብ ንቀው አይተውትም በማለት ሊያግባቧቸው ይሞክራሉ። ፕሬዘዳንታችንም አንተ ደደብ ትለዋለህ እንጂ ህዝቡ ደደብ አይደለም አንጀት አቁሳይ ነው። ብለው ይማረራሉ።በዚህ ግዜ ጠቅላይ ሚንስትሩ የሕዝቡን ደደብነት ለማረጋገጥ ከፈለጉ ነገ አብረን ከተማ ወጥተን አሳይዎታለሁ ይሉና በዚሁ ይስማማሉ። በማግስቱም ራሳቸውን ለውጠው ወደ ከተማ ይሄዱና ትንሽ ዘወርወር ብለው ሻይ ብና ሊሉ አንድ ከፍተኛ ሆቴል ሲገቡ ያማረ ሱፍ የለበሰ ሰው በር ላይ ቆሞ እጅ ነስቶ ይቀበላቸውና ባዶ መቀመጫ አሳይቷቸው ተመልሶ በሩ ላይ ይቆማል። ጠቅላይ ሚንስትራችን ሰውየው እንደዛ ለብሶ በር ላይ መቆሙ አሰገርሟቸው እግረመንገዳቸውንም የህዝቡን ደደብነት ለፕሬዘዳንታችን ማረጋገጫ ይሆነኛል ብለው አስበው ሰውየውን ጠርተው ለምን በር ላይ ቆምክ ይሉታል።ሰውዬውም ምድብ ሠራዬን እየሰራሁ ብሎ ይመልሳል። ጠቅላይ ሚንስትሩም ምድብ ሠራህ ወይም በሆቴሉ ያለህ ሃላፊ ምንድነው ብለው ይጠይቃሉ። ሰውየውም ፕሬዘዳንት ነኝ ብሎ ሲመልስ ፕሬዘዳታችን ቱግ ብለው በመናደድ ጭራሽ ፊት ለፊት ታሰድበኝ በማለት ሲያጉተመተሙ ነገሩ ያላማራቸው ጠቅላይ ሚንስትር ሰውየው እንዳያቃቸው ቶሎ ብለው ሊያሰናብቱት 5 ብር ከኪሳቸው አውጥተው እንካ ቢሉት ሰውየውም መልሶ ይቅርታ ያድርጉልኝ ጌታው ምንም አይነት ገንዘብ መቀበል በሙስና ስለሚያስወነጅለኝ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሰጡልኝ እሱ ከፈቀደ ይሰጠኛል ካልፈቀደም ይቀራል ብሎ ይመልሳልቻዋል። ይህን የሰሙት ፕሬዘዳታችን ፉተታና ስድቡ በጠቅላይ ሚንስትሩም ላይ መድረሱ አስፈንድቋቸው ለመሆኑ የሆቴሉ ጠቅላይ ሚንስትር ደግሞ ማነው ብለው ይጠይቃሉ። ሰውየውም ወደ ገንዘብ ተቀባዩ እያመለከተ እሳቸው ናቸው በማለት ሲመልስላቸው። ፕሬዘዳንቱ በተራቸው እየሳቁ ጠቅላይ ሚንስትሩም እየተቃጠሉ ሁለቱም ሆቴሉን ለቀው ይወጣሉ። በመንገድ ላይም እየሄዱ ፕሬዘዳንቱ ህዝቡ ደደብ እንዳልሆነ አየህ አይደል በማለት ለማስተማመን ቢሞክሩም ጠቅላይ ሚንስትሩ ግን የህዝቡን ደደብነት ለማረጋገጥ እልህ ገብተው ቆይ አሳይሃለሁ ይሉና ተያይዘው አንድ ታክሲ ውስጥ ይገባሉ። እንደገቡም ጠቅላይ ሚንስትሩ ስማ ሹፌር እቤት እንዳልሁና እንደሌለሁ ማየት ስለምፈልግ በቀጥታ እቤቴ ውሰደኝ። ይሉታል ባለታክሲውም እሺ ጌታዬ ብሎ ሞተር አንቀሳቅሶ ጉዞ ይጀምራል። በዚህ ግዜ ጠቅላይ ሚንስትሩ የህዝቡን ደደብነት ማረጋገጫ እንዳገኙ ሳይጠራጠሩ በሆዳቸው እየሳቁ ዝም ብለው ይጓዙ ጀመር ባለታክሲውም ኮተቤ ወስዶ ይጥላቸውና ውርዱ ይላቸዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩም ሳቃቸውን አፍነው ቤቴ ደረስኩ ይሉታል። አዎ ጥቂት ነው የቀርዎት ከዚህ በኋላ ሌሎች ታክሲዎች ተጠቅመው ቤትዎ ይገባሉ ብሎ ሳንቲሙን ተቀብሎ ያወርዳቸዋል። እንደወረዱም ጠቅላይ ሚንስትሩ በሳቅ በመንከትከት አዩ ክቡር ፕሬዘዳንት የህዝቡን ደደብነት 1ኛ እዚሁ አጠገቡ እያለሁ እቤት መኖሬን ማየት እፈልጋለሁ ስለው እሺ አለ 2ኛ ቤትህ የትነው ብሎ እንኳን ሳይጠይቅ እዚህ አምጥቶ ጣለኝ፥ ከዚህ በላይ ምን ደደብነት አለ ብለው ከትብለው ሲስቁ። ፕሬዘዳንቱም ሳቅ ብለው ሹፌሩ አውቆሃል ባክህ ኮተቤ አምጥቶ ጥሎህ ከዚህ በኋላ ሌሎች ታክሲዎች ተጠቅመው እቤትዎ ይደርሳሉ ያለህ የክልል 4 የክልል 3 የክልል 2ና የክልል 1 ታክሲዎችን ይዘህ አስመራ ግባ ቤትህ አስመራ ነው ማለቱ ነው ።ብለው አሁንም ጠቅላይ ሚንስትሩ በመወረፋቸው ተደስተው ከት ብለው ከሳቁ በኋላ ከዚህ ሁሉ ጣጣ እቤት መኖር አለመኖርን አርፈህ ስልክህን ደውለህ ብታረጋግጥ ይሻል ነበር። ብለው እርፍ ። ደደብ ሲፈልጉ የዋሉት ጠቅላይ ሚንስትሩም በተራቸው ከት ብለው ስቀው የማታ ማታ ልፋቴን ቆጥሮ አንድ መጽናኛ እርስዎን ባይሰጠኝ ፉከራዬ ሁሉ መና ቀርቶ ነበር ብለው ሁለቱም እየተሳሳቁ ወደ መጡበት ሄዱ። |
