ጸሎተኛው ህጻን
|
ማሙሽ ከመተኛቱ በፊት አልጋው ሠር ተበርክኮ ሲጸልይ አባት ባጋጣሚ በማሙሽ መኝታ ክፍል በኩል አለፍ ሲል ያየውና ተገርሞ ድምጽ ሳያሰማ ማሙሽ ምን ብሎ እንደሚጸልይ ለመስማት ይቆማል። ማሙሽም ሲጸልይ "አምላኬ ሆይ እናቴን ጠብቅልኝ ፤ አባቴን ጠብቅልኝ የሴት አያቴን ጠብቅልኝ" ካለ በኋላ የወንድ "አያቴን ታ፤ታ" በማለት ጸሎቱን አሣርጎ ይተኛል። አባትም ልጁ በጸሎቱ መጨረሻ ላይ የወንድ አያቴን ታ፤ታያለው ነገር ሊገባው ባይችልም በልጁ ጸሎተኛ መሆን ብቻ ተደስቶ ያድራል። ጠዋት ሁሉም ከእንቅልፍ ሲነሱ የወንድ አያት ግን ሞተው ይገኛሉ።ሃኪም በልብ ድካም መሞታቸውን ቢያረጋግጥም አባት የማሙሽ ጸሎት ትዝብሎት ከሽማግሌው ሞት ጋር ይገናኝ ይሆን ብሎ ማሰቡ አልቀረም።ወዲያው ደግሞ አጋጣሚ እንጂ ምንም ግንኙነት ሊኖረው አይችልም ብሎ ይተወዋል። በሚቀጥለውም ቀን እንደተለመደው ተንበርክኮ ሲጸልይ አባት ተደብቆ ይሰማዋል።ማሙሽም " እናቴን ጠብቅልኝ ፤ አባቴን ጠብቅልኝ " ካለ በኋላ "የሴት አያቴን ታ፤ታ " በማለት ጸሎቱን አሳርጎ ይተኛል።አባትም በነገሩ እየተብከነከነ እንቅልፍ በአይኑ ሳይዞር ያድርና በማለዳ ተነስቶ የአሮጊቷን በሡላም ማደር ለማረጋገጥ ወደ አልጋቸው ቢሄድ ሞተው ያገኛቸዋል። አሁንም ሃኪም ልብ ድካም ብሎ ያረጋግጣል።አባት ግን የሚስቱን እናትና አባት በሁለት ቀን ውስጥ በተመሳሳይ ሁኔታ መሞታቸውን ከልጁ ያልተለመደ አይነት ጸሎት ጋር ግንኙነት ሳይኖረው አይቀርም የሚለውጥርጣሬው በርትቶበት ለሰውም ሳይነግር ብቻውን ይጨነቅ ጀመር። በሚቀጥለው ቀንም የማሙሽን ጸሎት ተደብቆ ሲሰማ ማሙሽ "አምላኬ ሆይ እናቴን ጠብቅልኝ ፤ አባቴን ታ፤ታ" ብሎ ጸሎቱን በአጭሩ ያደርስና ይተኛል።አባትም በሰማው ነገር ደንግጦ በተኛበት እንዳይሞት ቁጭ ብሎ ያድርና ገና ሲነጋጋ ወደ ዶክተር ሮጦ ሄዶ ልብ ድካም እንዳለበትና እንደ ሌለበት ለማወቅ ይመረመራል። ሃኪሙም ልብድካም እንደሌለበት ያረጋግጥለትና ወደ ቤቱ ሲመለስ ሚስቱ በር ላይ ቆማ በጭንቀት ስትንቆራጠጥ ይደርሳል። እሱም ምንሆነሻል ብሎ ይጠይቃል።ሚስትምድንጋጤዋ እንዳይታወቅ ተጠንቅቃ እንኳን መጣህልኝ ፍቅሬ ይኸውልህ ጉድ ሆነናል።ወተት አመላላሹ ወተቱን ሰጥቶኝ እኔም ወተቱን ገልብጨ እቃውን ልሰጠው ስመጣ ሞቶ አገኘሁት። ብላ ሶፋው ላይ የተንጋለለውን የወተት ሻጭ እሬሳ ስታሳየው ባልም ጉዳዩ ገብቶት ለካስ ልጄ የምለው ማሙሽ የወተት አመላላሹ ልጅ ኖሯል ብሎ ሚስቱን ገርፎ አባሮ ያለስጋት ብቻውን መኖሩን መርጧል።
|
