መሰረተ ትምህርት
|
የመሰረት ትምህርት ፕሮግራም እንዲስተምር የተመደበ አንድ ስልቹ አስተማሪ ሁል ጊዜ ከ ሃ እስከ ፐ ይጽፍና እሱ ሃ ሲል ተማሪዎቹ ሁ ሂ ሃ ሄ ህ ሆ በማለት እንዲዘልቁ ይነግራቸዋል ብቻ የመጀመሪያ ፊደል ሲጠራላቸው እንሱ እስከ መጨረሻው ያነበንባሉ።ለ ሲላቸው እስከ ሎ በ ሲላቸው እስከ ቦ ማነብነብ ብቻ አስተምርዋቸው ቃላትን ማንበብ ሳይችሉ የግምገማው ፈታኝ ይመጣል።አስተማሪውም ተማሪዎቹ ብቁ ናቸው ብሎ ሪፖርት አድርጎ ነበርና ፈተናው ደረሰ።ፈታኙም ከ ሃ እስከ ፐ ተናግሮ ሳይጨር እነሱ እስከ ፖ ሲያነበቡ በጣም ተደንቆ የፊደል ፈተናውን እንዳለፉ ቆጥሮ በቀጥታ ወደ ቃላት ፈተና ይገባል። በመጀመሪያ ከፋ የሚል ቃል ጽፎ ሲጠይቅ ተማሪዎችም በተማሩት መሰረት ከፍ ኩፍ ኪፍ ካፍ ኬፍ ክፍ ኮፍ ብለው በመመለስ 'ሰነፉን አስተማሪ አጋልጠው አረፉ።
|
