ማሙሽና የአውቶቢስ ሹፌሩ
|
አንድ ዕድሜው ከ 10 አመት የማይበልጥ ሞገደኛ ህጻን አውቶቢስ አስቁሞ ይሳፈራል። በቀጥታም ከሹፌሩ ጎን ባለው ወንበር ላይ ሄዶ ይቀመጥና ለቅሶውን ይጀምራል። " ወይኔ አባቴ ዝሆን ቢሆን ንዎሮ _ _ _ ወይኔ እናቴም ዝሆን ብትሆን ንዎሮ እኔም ይሄኔ ትንሽኘ ዝሆን እሆን ነበር " እያለ እየዬውን ያስነካዋል የአውቶቢሱ ሹፌር የማሙሽን ጤነኝነት ተጠራጥሮ ዝም ብሎ ይመለከታው ጀመር ማሙሽም ለቅሶውን በመቀጠል " ወይኔ አባቴ በሬ ቢሆን ንዎሮ እናተም ላም ብትሆን ንዎሮ እኔም ይሄኔ ጥጃ እሆን ነበር " እያለ ለቅሶውን ቀጠለ። የአውቶቢሱ ሹፌር " አንተ ልጅ ምን ሆነሃል ያምሃል ? " ይለዋል። ማሙሽም እንዳልሰማ ለቅሶውን ይቀጥላል። " ወይኔ እናቴ ግመል ብትሆን ንዎሮ አባቴ ግመል ቢሆን ንዎሮ እኔም ይሄኔ ትንሽዬ ግመል እሆን ነበር" እያለ ጭራሽ ድምጹን ክፍ አድርጎ እዬዬውን አስነካው። አሁን የአውቶቢሱ ሹፌር ማሙሽ እየተሞላፈጠ መሆኑ ይገባውና በቁጣ ሊያስቆመው አስቦ " ስማ አንተ ባለጌ ልጅ ዝም ብለህ ትጓዝ እንደሆን ተጓዝ አለበለዚያ አውጥቼ ነው የምወረውርህ " በማለት ድምጹን ጎርነን አይኑን ፈጠጥ አድርጎ ይቆጣዋል። ማሙሽ ግን አሁንም ቁጣውን እንዳልሰማ ድምጹን የበለጠ ከፍ አድርጎ የእንስሳት ስሞችን አንድ በአንድ እየጠራ ማላዘኑን ተያያዘው ። የአውቶቢሱ ሹፌር በማሙሽ አድርቅነት ብስጭትጭቱ ይወጣል። እንዳይመታው ሕጻን ነው። ከመኪና አውርዶ እንዳይጥለውም ህጉን ፈራ።እንዳይተወው ደግሞ ለቅሶው ረብሾት ደሙ በንዴት እየተንተከተከ አሁንም ማሙሽን ሊያስፈራር ቢሞክር ማሙሽ ምንም መልስ ሳይሰጠው ወይኔ እናቴ እንትን ብትሆን ንዎሮ አባቴ እትን ቢሆን ን ንዎሮ ማለቱን አላቆም አለ። ሹፌርም ከብስጭቱ የተነሳ እየተንቀጠቀጠ ንዴቱን በስድብ ሊያበርድ " ስማ ማሙሽ እናትህ ሸርሙጣ አባትህ ደግሞ ውዳቂ ሰካራም ቢሆን ንዎሮ ምን አንተ ምን ትሆን ነበር ? " በማለት ወደ ማሙሽ ዞሮ በጥያቄ ያፈጥበታል። እስካሁን መልስ ሳይሰጥ የቆየው ማሙሽም ለቅሶውን ቆም አድርጎ ፈገግ በማለት " የአውቶቢስ ሹፌር እሆን ነበር ብሎ " በንዴት የተንተከተከው ሹፌሩን አገንፍሎት አረፈው። አያድርስ ነው እንጂ ምን ይባላል።
|
