Back Home               Articles              Poems           News              Jokes               Email Us

        THIS WEBSITE IS CURRENTLY BLOCKED IN ETHIOPIA

 

ካልጠፋ ምራቅዎ!!


 

በጠ/ሚ ገምጋሚነት የተወካዮች ምክር ቤት አባላት እየተገመገሙ ሣለ  ጠ/ሚ ድንገት ሲጋራ ያልቅባቸውና የአማራውን ክልል ፕሬዘዳንት 10 ብር ሰጥተው ይህቺ ምራቅ ሳትደርቅ ሲጋራ ገዝተህ ብለው ይልኩታል; የአማራው ፕሬዘዳትም ምራቋ ሳትደርቅ ለመድረስ እንደ ንፋስ ብንንንንንንንንን እያለ ልቡ 999 እየመታ ሮጦ ገዝቶ ሲመለስ እንዳሰበው ሳይሆን ምራቋ ደርቃ ይደርሳል;;

ጠ/ሚም ቆጣ ብለው...<< ምን ነበር ያልኩት? ምራቋ ሳትደርቅ ብዬ አልነበርም >> ብለው ያፈጣሉ?

እሱም እየተንቀጠቀጠ
<<
ጌታዬ የዛሬን ብቻ ይቅርታ ይደረግልኝ>>  በማለት እየተለማመጠ ይመለሳል;;

ጠ/ሚርም <<< ይህን ብቻዬን መወሰን አልችልም ለምክር ቤቱ አቅረበዋለሁ >> በማለት ጉዳዩን ለፓርላማ ያቀርባሉ;

የኢሃዴግ አባሎች ሁሉ አዲሱ ለገሰን እየወቀሱ አስተያየት ከሰጡ በኋላ አንድ የተቃዋሚ ድርጅት መሪ እጃቸውን ያወጡና አስተያየት አለኝ ይላሉ;

ጠ/ሚርም እድል ይሰጣሉ ;

የተቃዋሚው ድርጅት መሪም ቀጠል አድርገው << አዲሡ ለገሰ አሁን ምን ኣጠፋ ብለው ነው ? የሮጠበት የልቡ ትርታ ከረባቱን እስኪያርገበግበው ድረስ እየታየ አሁን እሱን መቅጣት ተገቢ ነው? ጥፋቱ ያለው እርስዎ ጋ ! ከሞላ ምራቅዎ ምስር የምታክል ተፍተው እንጂ  በአፍታ መድረቋ እሱማ ምን አደረገ በማለት ጠ/ሚርን በአሽሙር አጠናፈሯቸው; ቁጭ.../.....