አባዬ ካፒታሊዝም ምን ማለት ነው ?
|
ልጅ አባቱን ካፒታሊዝም ማለት ምን ማለት እንደሆን እንዲያስረዳው ይጠይቃል።አባትም እንዴት አድርጎ ቢያስረዳው በቀላሉ ሊገባው እንደሚችል ትንሽ አሰብ አድርጎ እንዲህ ይገልጽለታል።አየህ ልጄ ካፒታሊዝም ማለት አንዱ በገንዘቡ ብዙዎችን የሚቆጣጠርበት ሠርኣትነው። ባለገንዘቡ ካፒታሊስት ይባላል። በካፒታሊዝም ሠርኣት መንግስት ህዝብን የሚያስተዳድርበት ሠልጣንና ገንዘብ የሚያገኘው ከካፒታሊስቱ ስለሆነ ካፒታሊስቱ ሡራተኛውን ክፍል እንደፈለገ ቢያደርግ ምንም አይል።ህዝብም በደሉን እያየ ምንም ማድረግ ስለማይችል ዝም ይላል። ለምሳሌ የኛን ቤተሰብ እንደ ካፒታሊዝም ሠርኣት ብንወስደው እኔገንዘብ ስለማመጣ ካፒታሊስት ነኝ። እናትህ ደግሞ ገንዘቡን ተኔ ተቀብላ ቤተሰቡን ስለምታስተዳድር መንግስት ማለት ነች።አንተና ወንድሞችህ ደግሞ ህዝብ ስትሆኑ= ሞግዚታችሁም ሡራተኛው ክፍል መሆኗ ነው።ብሎ በምሳሌ ያስረዳዋል። ልጅም የአባተን አገላለጽ በማንሰላሰል ውሎ ይመሽና ይተኛል።አልጋውም ላይሆኖ ሲያስብ ቆይቶ እንቅልፍ ሸለብ እንዳደረገው ድንገት የሚንጓጓ ድምጽ ይሰማናብንን ብሎ እናትና አባቱ ወድተኙበት አልጋ አቅጣጫ ሲመለከት እናቱ ብቻኘ ተኝታ ያያል።አባቱን በአይኑ ሲያፈላልግ የሚንጓጓው ድምጽ አሁንም ከወደ ሞግዚቷ ክፍል ተሰማው ። ኘቀስ ብሎ ሄዶ በጭላንጭል ሲመለከት አባቱ በሞግዚቷ ላይ ሰፍሮ ያየዋል። ልጅም የአባቱን ነውርኘ መመልከቱ እንዳይታወቅበት ቀስ ብሎ ኮቴ ሳያሰማወደ መኝታው ይመለሳል።በማግስቱም አባቱና እናቱ በተቀመጡበት ይሄድና አባቱን እንዲህ ይለዋል አባዬ ትናት ስለ ካፒታሊዝም ያስረዳኸኝ አሁን ገና በደምብ ገባኝ ሲለው አባትም ደስብሎት ጎሽ ልጄ እስኪ እንዴት እንደገባህ ንገረኝ ይለዋል። ልጅም ሲያስረዳ፥ አንተ እንዳልከው ካፒታሊዝም ሰራተኛውን ክፍል እየተጫነው ሲያጠቃው መንግስት ዝምሎ ተኛ። ህዝብ ደግሞ ምንም ማድረግ ስለልቻለ በደሉን አይቶ ዝም አለ ብሎ ሳይጨርስ በቃ በቃ ልጄ በደምብ ገብቶሃል በቃ ጎሽ ጎሽ ብሎ ጉዱን ሚስቱ ሳትሰማ የልጁን አፍ አዘጋ እላችኋለሁ። ታዲያ ይህን ገጠመኝ የትኛው ተረት ይገልጸዋል ይላሉ 1 ቁጭ ብለው የሰቀሉት ቆመው ማውረድ ያስቸግራል 2 በለው ብሎ ብትር ሰጠው መጀመሪያ ራሱን ለመጠው 3 ሳይቃጠል በቅጠልከ 4 አፍ ከወጣ አፋፍ 5 በለፈለፉ በአፍ ይጠፉ 6 ከልጅ አትጫወት ይወጋሃል በእንጨት
|
