Back Home               Articles              Poems           News              Jokes               Email Us

        THIS WEBSITE IS CURRENTLY BLOCKED IN ETHIOPIA

 

 የቀድሞዋና የአሁንዋ የኢትዮጵያ
ፈርስት ሌድዮችየስልክ ውይይት


 

ውባንቺ "ሃሎ ወይዘሮ አዜብ እንደምነሽ ?"

አዜብ "ደሃን ደሃ ማን ልበል ?"

ውባንቺ " ከሃራሬ ነው የምደውለው ውባቺ ነኝ የቀድሞው የኢሰፓ ዋና ጸሃፊ የአቢዮታዊ ጦር ጠቅላይ ዋና አዛዥ የሚንስትሮች ምክርቤት ሰብሳቢ የጓድ ሊቀመንበር _ _ _

አዜብ "ዋይ _ _ _! ግደፊ በቃ ተረዳሁሽ ቀዳሚ ጠርናፊው ምሽት ነኝ አትይም "

ውባንቺ "አዎ ነኝ"

አዜብ "ሃራይ ምን ፈለግሽ ?"

ውባንቺ " እንጦጦ ማሪያም ሠለት ሠላለብኝ ልመጣ አስቤ ነበር ባለቤትሽን ታስፈቅጅልኛለሽ? "

አዜብ " ሃራይ ቆይ አንዴ ጠብቂ ልጠይቀው"

አዜብ " ሠለትሽ ምንድነው? ይላል"

ውባንቺ " አንድ ኪሎ ወርቅ"

አዜብ "ደህና መቀሌ ማሪያም ነው የምታስገቢ"

ውባንቺ " እንዴ እኔ የተሳልኩት ለእንጦጦ ብዬ እኮ ነው"

አዜብ " ! ጠርናፊዋ የመቀሌ ማሪያም ነች ብዬሻለሁ"

ውባንቺ " አሁንስ አይን አወጣችሁ ደግሞ እመቤታችንንም ልትከፋፍሉ።የናተን ጉድ ቁሉቢው ገብርኤል ያሳየኛል"

አዜብ " ! ምን የማይርዳት ነቺ ይቺ አለ ጠርናፊው አለ ክልልሽ አትሳይ "

ውባንቺ " እሞታታለሁ እንጂ ለናተ ወርቄን አልሰጥም "

አዜብ "ሙቺ ምን አገባኝ ዋ ! እንክዋን አንቺ ህዋአትም ሞትዋል"

ውባንቺ " ደርሷል ጊዜው ግዴለም ግዴለም _ _ _ "

አዜብ " በይ ባክሽ አንቺ ሠራ ፍትነሽ ካንቺ ጋ ስዛረብ ወጤ እንዳይጎረናና እንዳታስገመግሚኝ "

ውባንቺ " ደግሞ በየትኛው ሙያሽ ነው ወጥ የምትሰሪው _ _ _? "ቂቂቂ

አዜብ " ዝበይ አንቺ ትምክህተኛ የትምክህተኛ ምሽት "

ውባንቺ " አይ ሙያውን እንኳ ለኛ ተይው አንቺ አርፈሽ ስኳርሽን ቃሚ "

አዜብ " ! የበርሃው ነው የምትዛረቢ አሽርተ አመት እኮ አለፈው"

ውባንቺ " ቢሆንም በአሕድን ማእከላዊ ኮሚቴ ካልተረዳሽ ብቻሽን ወጥ መስራት አትችይም ለመሆኑ የቤተመንግስቱን የጠጅ በርሜሎች ጠጅ ተጥሎባቸው ያውቃሌ?"

አዜብ " ! ወዲ ጎላ ! የትምክህተኛ መጠጥ ልጠጣ ፈለግሽ?"

ውባንቺ " ምን በወዴሣሽ አንዴኃ በፎሖቦሽን በጥብጪና ጠጪ እንጂ ታየኝ ያ የጠጅ በርዳሜል የዱዳቄት እዳቃ መስሎ"

አዜብ " አንቺ ምላሳም ነሽ ዋ ! _ _ _ አሽርት አመት አለፈ አልኩሽ ከበርሃ ከወጣሁ አልተረዳሽም ዋ ! የሂልዳተን ዳከዴዪክ ዳማ ሊበላው እዳነዴዪ በፎሖቦ እጠጣለሁ ?"

ውባንቺ " ቂቂቂ _ _ _ አምባሻም የኬኮች ጠርናፊ ሆኖ ሂልተን ገባ እንዴ? "

አዜብ " እዋ ! ይቺ ሴት ምላስ እሳት። ተስፋ ቆረጥሽ ስድብ አበዛሽ

! ቁምነገር ተዛረቢ እዋይ ! "

ውባንቺ " እሺ እሺ ለመሆኑ ለኢትዮጵያ ህዝብ ምን አስባችሁለታል?"

አዜብ " አሁን ደህና አልሽ። አልሰማሽም እንዴ ሃውልቱ ከጣሊያን ልናስመጣ በጥድፊያ ላይ ነን"

ውባንቺ "አዎ ሰምቻለሁ ዳቦ ለጠየቀው ህዝብ ድንጋይ በጥድፊያ ልታስመጡ"

አዜብ " አንቺ ግደፊ የ 3000 አመት ታሪክ ዋይ ! _ _ _ ድንጋይ አትበይ"

ውባንቺ " አለቃ አምባቆም ያሉትን ልንገርሽ

የብዙ ሺህ ዘመን መሆኑ ተረስቶ

ወያኔ ቆጠረው በመቶ በመቶ" ነበር ያሉትን።

አዜብ " ጠባቦች ናቸው በመቶ የቆጠሩት አሁን ጠባብ የለም ተረዳሽ? "

ውባንቺ " እሺ እሺ እረስቼው ነው ሌላስ ምን አሰባችሁለት ለህዝቡ ?"

አዜብ " ሌላ ሪፖርተር ጋዜጣ አንብቢ "

ውባንቺ " እኔ እንክዋን የማገኘው ጦቢያን ነው "

አዜብ " ጦቢያ ጸረ ህዝብ ነው አታንብቢ"

ውባንቺ " በይ እንግዲህ ጓድ ሊቀመንበር መነሻቸው ደርሷል እኔም ልሂድ መቀሌም መጥቼ ወርቄን አልሰጥ ሲያምርሽ ይቅር።

አዜብ " እኔ ወዲ ጎላ ነኝ ያንቺ አንድ ኪሎ ወርቅ ሲያምረኝ የሚቀረው ዋ! ውሻዬንም ብፈልግ በወርቅ አስራለሁ ዋይ አንቺ ሴት አዶላ ጨው መሰለሽ የሚወጣው?"

ውባንቺ " ደህና ሰንብቺ ታጋዳላይ አዜብ "

አዜብ " በይ ድሃን ሰንብቺ ግዋዲት ውብ አንቺ እዋይ ምላስ እሳት"