የቀድሞዋና የአሁንዋ የኢትዮጵያ
ፈርስት ሌድዮችየስልክ ውይይት
|
ውባንቺ "ሃሎ ወይዘሮ አዜብ እንደምነሽ ?" አዜብ "ደሃን ደሃ ማን ልበል ?" ውባንቺ " ከሃራሬ ነው የምደውለው ውባቺ ነኝ የቀድሞው የኢሰፓ ዋና ጸሃፊ የአቢዮታዊ ጦር ጠቅላይ ዋና አዛዥ የሚንስትሮች ምክርቤት ሰብሳቢ የጓድ ሊቀመንበር _ _ _ አዜብ "ዋይ _ _ _! ግደፊ በቃ ተረዳሁሽ ቀዳሚ ጠርናፊው ምሽት ነኝ አትይም " ውባንቺ "አዎ ነኝ" አዜብ "ሃራይ ምን ፈለግሽ ?" ውባንቺ " እንጦጦ ማሪያም ሠለት ሠላለብኝ ልመጣ አስቤ ነበር ባለቤትሽን ታስፈቅጅልኛለሽ? " አዜብ " ሃራይ ቆይ አንዴ ጠብቂ ልጠይቀው" አዜብ " ሠለትሽ ምንድነው? ይላል" ውባንቺ " አንድ ኪሎ ወርቅ" አዜብ "ደህና መቀሌ ማሪያም ነው የምታስገቢ" ውባንቺ " እንዴ እኔ የተሳልኩት ለእንጦጦ ብዬ እኮ ነው" አዜብ " ዋ ! ጠርናፊዋ የመቀሌ ማሪያም ነች ብዬሻለሁ" ውባንቺ " አሁንስ አይን አወጣችሁ ደግሞ እመቤታችንንም ልትከፋፍሉ።የናተን ጉድ ቁሉቢው ገብርኤል ያሳየኛል" አዜብ " ዋ ! ምን የማይርዳት ነቺ ይቺ አለ ጠርናፊው አለ ክልልሽ አትሳይ " ውባንቺ " እሞታታለሁ እንጂ ለናተ ወርቄን አልሰጥም " አዜብ "ሙቺ ምን አገባኝ ዋ ! እንክዋን አንቺ ህዋአትም ሞትዋል" ውባንቺ " ደርሷል ጊዜው ግዴለም ግዴለም _ _ _ " አዜብ " በይ ባክሽ አንቺ ሠራ ፍትነሽ ካንቺ ጋ ስዛረብ ወጤ እንዳይጎረናና እንዳታስገመግሚኝ " ውባንቺ " ደግሞ በየትኛው ሙያሽ ነው ወጥ የምትሰሪው _ _ _? "ቂቂቂ አዜብ " ዝበይ አንቺ ትምክህተኛ የትምክህተኛ ምሽት " ውባንቺ " አይ ሙያውን እንኳ ለኛ ተይው አንቺ አርፈሽ ስኳርሽን ቃሚ " አዜብ " ዋ ! የበርሃው ነው የምትዛረቢ አሽርተ አመት እኮ አለፈው" ውባንቺ " ቢሆንም በአሕድን ማእከላዊ ኮሚቴ ካልተረዳሽ ብቻሽን ወጥ መስራት አትችይም ለመሆኑ የቤተመንግስቱን የጠጅ በርሜሎች ጠጅ ተጥሎባቸው ያውቃሌ?" አዜብ " ላ ! ወዲ ጎላ ! የትምክህተኛ መጠጥ ልጠጣ ፈለግሽ?" ውባንቺ " ምን በወዴሣሽ አንዴኃ በፎሖቦሽን በጥብጪና ጠጪ እንጂ ታየኝ ያ የጠጅ በርዳሜል የዱዳቄት እዳቃ መስሎ" አዜብ " አንቺ ምላሳም ነሽ ዋ ! _ _ _ አሽርት አመት አለፈ አልኩሽ ከበርሃ ከወጣሁ አልተረዳሽም ዋ ! የሂልዳተን ዳከዴዪክ ዳማ ሊበላው እዳነዴዪ በፎሖቦ እጠጣለሁ ?" ውባንቺ " ቂቂቂ _ _ _ አምባሻም የኬኮች ጠርናፊ ሆኖ ሂልተን ገባ እንዴ? " አዜብ " እዋ ! ይቺ ሴት ምላስ እሳት። ተስፋ ቆረጥሽ ስድብ አበዛሽ ! ቁምነገር ተዛረቢ እዋይ ! " ውባንቺ " እሺ እሺ ለመሆኑ ለኢትዮጵያ ህዝብ ምን አስባችሁለታል?" አዜብ " አሁን ደህና አልሽ። አልሰማሽም እንዴ ሃውልቱ ከጣሊያን ልናስመጣ በጥድፊያ ላይ ነን" ውባንቺ "አዎ ሰምቻለሁ ዳቦ ለጠየቀው ህዝብ ድንጋይ በጥድፊያ ልታስመጡ" አዜብ " አንቺ ግደፊ የ 3000 አመት ታሪክ ዋይ ! _ _ _ ድንጋይ አትበይ" ውባንቺ " አለቃ አምባቆም ያሉትን ልንገርሽ የብዙ ሺህ ዘመን መሆኑ ተረስቶ ወያኔ ቆጠረው በመቶ በመቶ" ነበር ያሉትን። አዜብ " ጠባቦች ናቸው በመቶ የቆጠሩት አሁን ጠባብ የለም ተረዳሽ? " ውባንቺ " እሺ እሺ እረስቼው ነው ሌላስ ምን አሰባችሁለት ለህዝቡ ?" አዜብ " ሌላ ሪፖርተር ጋዜጣ አንብቢ " ውባንቺ " እኔ እንክዋን የማገኘው ጦቢያን ነው " አዜብ " ጦቢያ ጸረ ህዝብ ነው አታንብቢ" ውባንቺ " በይ እንግዲህ ጓድ ሊቀመንበር መነሻቸው ደርሷል እኔም ልሂድ መቀሌም መጥቼ ወርቄን አልሰጥ ሲያምርሽ ይቅር። አዜብ " እኔ ወዲ ጎላ ነኝ ያንቺ አንድ ኪሎ ወርቅ ሲያምረኝ የሚቀረው ዋ! ውሻዬንም ብፈልግ በወርቅ አስራለሁ ዋይ አንቺ ሴት አዶላ ጨው መሰለሽ የሚወጣው?" ውባንቺ " ደህና ሰንብቺ ታጋዳላይ አዜብ " አዜብ " በይ ድሃን ሰንብቺ ግዋዲት ውብ አንቺ እዋይ ምላስ እሳት" |