የአንበሣ ግቢ ማስታወቂያዎች


 

ድሮ ድሮ በአጼ ሃ/ሥላሴ ዘመነ መንግስት በ 6 ኪሎ አንበሳ ግቢ ውስጥ
የተለጠፈው ማስታወቂያ

እባካችሁ ጎብኝዎቻችን

የአንበሶቹ ምግብ በጥናት የሚዘጋጅ  በመሆኑ ከውጭ ምግብ እምጥታችሁ እንዳትመገቡዋቸው እንጠይቃለን!
የዘውድ አርማችን ናቸውና እናክብራቸው""
የሚል ነበር አሉ።


ይሀው ማሳሰቢያ በደርግ ዘመን ተለውጦ

ጥብቅ ማስጠንቀቂያ

ንበሶቹ የህዝብ ንብረት ናቸው። በመሆኑም ምግባቸውን የበላ ጎብኚ ከጸራ አብዮተኛ ተነጥሎ ስለማይታይ! አብዮታዊ እርምጃ ይፈጸምበታል!!
ግዚያዊ ወታደራዊ መንግስት


በዘመነ ወያኔ ደግሞ

የጨረታ ማስታወቂያ

መንግስት የግል ባለሃብቶችን ለማበረታታት እያደረገ ባለው የህዝብ ድርጅቶችን ለጨረታ አቅርቦ የመሸጥ እንቅስቃሴ መሰረት እነኚህን አንበሶች በቅርቡ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፤። ፡ አንበሶቹን የግል ሃብት ለማድረግ የምትፈልጉ ባለሃብቶች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።

ይላል