አበሻ ነህ እንዴ ?!

 

መቼም ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የመግባት ዕድል ማግኘት ማለት ምን ያህል አስደሳች እንደሆነ ለብዙዎቻችን የሚጠፋ አይደለም። ይሁን እንጂ ደስታውኘ የሚመነጨው በምቾትና በድሎት ለመኖር ካለው ጉጉት ሳይሆን ሡርቶ ራስን ለመቻል ካለው ተስፋ ይመስለኛል። ታዲያ አንድ እንዲሁ ሡርቶ ራሱን ለማስተዳደርና ድሃ ቤተሰቦቹን ለመርዳት ይጓጓ የነበረ ወጣት ጸሎቱ ሰምሮ D. V ይደርሰውና አሜሪካ ይገባል። ለመስራት ካለው ጉጉት የተነሳ አሜሪካንን ከረገጠበት ቀን ጀምሮ ሠራ ማፈላለጉን ተያያዘው። ዕድል አልቀና ብሎት ለረዥም ግዜ ያለስራ መቀመጥ በመገደዱ ይጨነቅ ጀመር። ይህንን ጭንቀቱን ያየ አንድ ሰው በዛው አካባቢ ወደሚገኝው Zoo ሄዶ እንዲሞክር ይነግረውና ይሄዳል። Zoo ውስጥ ገብቶም ሠራ አላችሁ ወይ ብሎ ይጠይቃል።

ኘበአግጣሚም ምንም የሠራ ልምድ የማይጠይቅ የግማሽ ሰአት ሠልጠና ብቻ የሚያስፈልገው ሠራ ያገኛል። ሠራው ምን መሰላችሁ? የዱር አራዊት ምስል አጥልቆ በብረት አጥር ውስጥ ገብቶ እንደተመደበበት አራዊት መሆን ነው። አጅሬም በአጋጣሚ የተመደበው እንደ ጎሬላ ዝንጀሮ ሆኖ እንዲሡራ ነበርና የተሰጠውን የ 30 ደቂቃ ስልጠና በብቃት አጠናቆ ፥ እንደ ዝንጀሮ መንጎማለል ፤ መጮህ ፤ መፈናጠር ብቻ ምን አለፋችሁ ሁሉን ሁሉን መሆን ችሎ ወደ ሠራው ተሰማራ። ጠዋት ሄዶ እስከ ማታ በብረት አጥር ውስጥ ሲንጎማለል ውሎ ማታ ወደ ሰውነቱም ወደቤቱም ይመለሰል።

 ረዥም ሰአት ስለሚሰራና ክፍያውም ጥሩ ስለሆነ በአጭር ግዜ ውስጥ ይጓጓለት የነበረውን ሁሉ በእጁ ማስገባት በመቻሉ ጭንቀቱ ወደ ፈጹም ደስታ ተለውጠ። ሠራውንም ተላመደው። ታዲያ መቼም በየቀኑ ለ12 ሰአት ከአራዊት መንጋ ጋር መዋል ቀላል አይደለም። አራዊት አራዊት ነውና ሳት ብሎ የሾለከ ቀን አያድርስ ነው። አጅሬም በተለይ ከጎኑ ባሉት አንበሶች እንደተሳቀቀ ነው፤

የፈራው አልቀረም አንድ ቀን በአንበሳውና በሱ መካከል ያለው በር ሳይዘጋ ተረስቶ ኖሮ አያ አንበሴ ጎልመም ጎልመም እያለ ወደ እሱ ሲመጣ፥ አጅሬ ዝንጀሮነቱን እረስቶ "ወይኔ ጉዴ ወይኔ ምነው በቀረብኝ" እያለ በጭቀት የሚገባበት ጠፍቶት አንዱ ጥግ ብረት ላይ ይለጠፋል። አፉን አውጥቶ እንዳይጮህ ጎብኝዎች ስላሉ ተቸግሮ፤ በጭንቅ ውስጥ እንዳለ ሳያስበው "ገብርኤል አውጣኝ " ሲል፥ አንበሳው ድንገት ቆም ብሎ። "እንዴ _ _ _! አበሻ ነህ እንዴ ?! "ብሎት እርፍ፥ ለካስ አያ አንበሴም የኛው ሰው ነበረ። ድሮስ ለአንበስነቱ ማን ብሎን አትሉም።ዝንጀሮነተሙ የንእጀራ ነገር ሆኖ እንጂ _ _ _ _ _።