|
ሦሥት አይነት ጋዜጠኞች አሉ |
|
3 አይነት ጋዜጠኞች አሉ 1ኛው አይነት ጋዜጠኞች ወሬን ከመንግስት አፍ ወደ ሕዝብ ጆሮ በማመላለስ የሚሰሩ ውጤታማነታቸው የሚለካው ሕዝብን ለመንግስት ለማስገዛት በቻሉበት መጠን ነው ፤ እነኚህ ጋዜጠኞች ህያው የመንግስት መገልገያ በሚል ተቀጥላ ስም ይታወቃሉ; 2ኛው አይነት ጋዜጠኞች በአንድ የፖለቲካ ድርጅት ጥላ ስር ተከልለው ወሬን ከድር ጅቶቻቸው ወደ ሕዝብና ወደ መንግስት በማመላለስ የሚሰሩ ሲሆኑ ውጤታማነታቸው የሚለካውም የቆሙለት ድርጅት አላማ ግብ ለመምታት በቻለበት መጠን ነው; እነኚህ ጋዜጠኞች አድማሰ ጠባብ ጋዜጠኞች በሚል ተቀጥላ ስም ይታወቃሉ፤
3ኛው አይነት ጋዜጠኞች ወሬን ከህዝብ ወደ መንግስትና ወደሚመለከተው አካል እያ መላለሱ የሚሰሩ ውጤታማነታቸው የሚለካው
በህዝብ የማህበራዊ ህይወት ሁለንተናዊ እድገት ለማሳየት በቻለበት መጠን ነው፤ እነኚህ ጋዜጠኞች የህዝብ እንባ ጠባቂ በሚል
ተቀጣላ ስም ይታወቅሉ;
|