|
ውሃ ያጣ መስኪን ዘላን ሃገር ለሃገር እንደሚዞር
እግሬ እንደ ወሰደኝ ሄጄ ደግሞ የጣለኝ ጥግ ማደር
ለኔም እጣ ክፍሌ ሆኖ የአርባ ቀን እድሌ ቅምር
ይሀው አልሁ እድሜ ልኬን በዋልኩበት ሳላድር
ማልጄ ድንኳን ስነቅል ድግሞ ምሽቱን ስወጥር
እንደ ሰው ለኔም ወግ ደርሶኝ ጎጆ ቀልሼ ባላውቅም
ቤት ላእንቦሳ ባይ እንግዳ- ደጄን ባያጥለቀልቀም
ኩሩ ኢትዮጵያዊ ንኝና ባህሌን ፍጹም አለቅም
እናም እንሆ ራእይዎች ቤት ለእንቦሳ ብያለሁኝ
ማስሪያም የለኝምና እንቦሳ እስራችሁ ይቅርብኝ
እንዲሁ ደግሞ አንዱን ቀን እገሬ ሲመራኝ መጣለሁ
አድራሻ የሌለው ዘላን ቀጠሮ አይዝም አውቃለሁ
እንዲሁ እገሬ ሲመራኝ አንዱን ቀን ደግሞ መጣለሁ
|