Poems ግጥም
Back Home Articles Poems News Jokes Email Us
THIS WEBSITE IS CURRENTLY BLOCKED IN ETHIOPIA
ይህን አልክ አትበለኝና እና አንተ አንድዬ ፈጣሪ የይድረስ ይድረስ ጠፍጥፈህ ስንኩል የፍጡር ቅራሪ በሰው አምሳል ተንገላዋጅ የቁም በድን ትቢያ አዳሪ ምን ነበር ጤና ባትነሳው ሰላማዊውን ምስኪን ሰው ? ጭንጋፍ ላይ ከምተነፍስ ሽሉን በሾተል ብትመታው አልያም መጀመሪያውን የይድረስ ይድረስ ባትሰራው እንደ አውሬ ከርሱን አስፍተህ ምንአለ እራስ ባትነሳው ?