|
ይባል ነበር ድሮም የተገላቢጦሽ አህያ ወደ ሊጥ ውሻ ወደ ግጦሽ፥ ዘንድሮ ግን ባሰ ጠፋለት ለከት፤ አራዊት አልቀረ የቤት እንስሳት፤ ተገለባበጠ የሁሉም ድርጊት፥ አንበሳ እንደ አህያ ተጫነ ዳውላ፥ ነብር በረት ታስሮ ጭድ አተላ በላ፥ አህያ ከጅብ ጋር ገበታ ቀረበች፥ ጥምባ ጥምቡን ወዳ ሰርዶ ላይንዋ ጠላች፥ ቀበሮም እንደ በግ ብርግግ ብርግግ አለች፥ የዱር አርዊቱን እንስሳቱን ሁላ፤ አባራ አድና ደም መጥጣ ዘንጥላ፤ ፍየል ሆነች አሉ ሙዳ የምትበላ፥ እሷው ግጣ ግጣ ቅልጥም ብትጥልለት፤ ጅብ አህያን አጭቶ ጥሎሽ አገባላት፥ ይሄ ግልብጥብጦሽ ያበቃለት ለታ፤ አንበሳ ነብሩ ቀበሮው ሲፈታ፥ ፍየልን አያርገኝ መትረፊያም የላት፥ የአንበሳም አይደለች የቀበሮ ናት፥ ነብርና አንበሳም የድርሻቸውን፤ አንዱ ደደቢቷን አንዱም ከርሳሙን በ ሳ . አ
|