Poems                                                 ግጥም

  Back Home      Articles          Poems           News              Jokes               Email Us

        THIS WEBSITE IS CURRENTLY BLOCKED IN ETHIOPIA

ምን መንፈስ ይሆን ሹክ ያላት?
 

                                       
                                              
                                   

ያቺ የአንድዬ ምሩቋ - ቀለም ያልገባት እናቴ

አጥና ልጄ ትለኝ ነበር - ፊደል አቅርባ ከፊቴ

ለየኔታ ትከፍለው ዘንድ -አንድ ሽልንግም ቸግሯት

ከእውቀት ገበያ ቀርቼ -ልጅዋ ከቤት ብውልባት

ልቧ በቁጪት በልዞ - የምታደርገው ቢጠፋት

ያቺ የአንድዬ ምሩቋ -ቀለም ያልገባት እናቴ

በል ልጄ ትለኝ ጀመር -ፊደል አቅርባ ከፊቴ

በቃል ፊደል ቆጠራዋም ከ እስከ እየደገመች

በጠቋሚው ስንደዶዋ ከ እስከ እየተመመች

በል ልጄ ትለኝ ጀመር - በሳሩ ' እያሳይች

ፊደል አለመለየቷን - ጪንቀቷን መች ተረድቼ

ማለቴን ቀጠልኩ እንጂ - ጣቴን በ "ላይ ሰክቼ

በአሻሮ ጪስ ተጨናብሳ - ምስኪኗ እምዬ የኔ እናት

ያቺ መከረኛ ሽልንግ - ከመዳፍዋ ስትገባላት

ወደ የኔታ ስትወስደኝ - መቼ በወጉስ ነጋላት

 

ከአናት እየጠቆሙ በል ሲሉኝ የኔታ

እኔም ከእናቴ ባወቅኩት ን እየጠቆምኩ ሳምታታ

በቁንጥጫ መዠለጉኝ - ጭኔ ከእንጆሪ እስኪቀላ

ሚጢጢዋ ልቤ አዝና -መፈጠርዋን እስክትጠላ

ፊደል አለመለየቷን - ችግሯን መች አውቄላት

አስቆነጠጥሽኝ ብዬ እንጂ - የቁም ስቅሏን ያሳየኋት

ታዲያ ለዚህች ለናቴ ፊደል ላልዘለቀች ምስኪን

ምን መንፈስ ይሆን ሹክ ያላት እውቀት ብሩህ ተስፋነቱን ?

ያቺ ያንድዬ ምሩቋ -ቀለም ያልገባት እናቴ

አጥና ልጄ ትለኝ ነበር - ፊደል አቅርባ ከፊቴ

ሳ/አ