Poems                                                 ግጥም

  Back Home      Articles          Poems           News              Jokes               Email Us

        THIS WEBSITE IS CURRENTLY BLOCKED IN ETHIOPIA

             
ምንድነው ሙስና ?

                                       
                                              
                                 

መጠጡ ቦንማሮ ምሱ ነጭ የደም ሴል፤

በአቡን መስቀል ውግረት የማይለቀው ጋኔል

እንደ ቅስም ሰባሪው እንደ አሰልስሉ ኤድስ፤

ገዝግዞ የሚቀስፍ ሌላ አዲስ ቫይረስ _ _ _ ፤

ይሆን እንዴ ? ይሄም _ _ _ ሙስና የሚሉት

አዲስ ባላጋራ ሌላ አስከፊ ጠላት

ዛዲያማ ምንድነው ? ሃገሩን ያመሰው _ _ _ ?

ሹማምንቱን ሁሉ ነድፎ ነድፎ የጣለው ?

አልኩና የኔታ መምሬን ጠየኩኝ

የሙስናን ምስጥር ገልጸው እንዲያስረዱኝ፥

ጥቂት አሰብ አርገው ነገሩን በእርጋታ፥

እንድህ አሉ የኔታ _ _ _ _

አጀክቲቭ ና በርብ ነጮቹ እንደሚሉት፥

ሙስና ቅጽሉ ግሱም ሙሰኝነት ፥

ሙሰኛም ስሙ ነው ናውን የሚባለው፥

አጠቃቀሙ እንጂ ቃሉማ ያው ቃል ነው፥

ትርጉሙም ጉቦኛ ፤ አፍቃሪ ነዋይ ነው፥

ቃሉማ ያው ቃል ነው ።

_ቀሳፊም አይደለ አሰልስሎም አይገድል፥

ባህሪ ነው እንጂ እንድያው አጉል አመል

አይተላለፍም ፤ ተዛማችም አይደል።

ብለው ሲገልጹልኝ የሙስናን ትርጉም ፥

ደግሜ ጠየኩኝ ያልገባኝ ነገር፥

_ታዲያ ለምንድነው ባገሩ በሙሉ ፥

ሙሰኝነት በዛ ተስፋፋ መባሉ ?

በደም በንክኪ አይስፋፋም ካሉ ፥

ለምን ይሆን ታዲያ ትልልቁ ሁሉ ፥

ሙሰኛ ተብሎ ከሰው መገለሉ _ __ _ ?

አልኩና ጠየኩኝ ግልጽ እንዲሆንልኝ፥

ቃጠሉ የኔታ

እኔም ሰምቻለሁ እንዲህ ያለ ነገር ፥

ከወደ አፍሪካ ቀንድ ከሸገር ሲነገር፥

ሙዳሰኝዳነት ዳነግፎሖቦ ዳሰውን ሁሉ እንደዳሚያስር፥

ግና እኔ እስከማውቀው ሙሰኝነት ቃል ነው

ቫይረስ ሆነ ካሉም አድራጊው ያው ሰውነው

ቃሉማ ያው ቃል ነው፥

ምናልባትም ደግሞ በዝያች ምስኪን ሃገር

ተዛምቶ ሠር ሰዶ ድብቅ የደም ካንሰር፥

እራስ ላይ እስኪዘልቅ ያለተደረሰበት ፥

በሽታ ይኖራል ህዝቡ ያለቀበት፥

በደካማ ብልት በጉፋን በእንቅፋት ፥

አሳቦ እንደሚጥል እንደ ኤድሱ አይነት

ሙሰኝነት መስሎ ህዝቡን የሚጨርስ ፥

አውራ የደም ካንሰር አደገኛ ቫይረስ፥

ቢኖር እንጂ እዛም ህዝቡን የጨረሰው፥

ቃሉማ ያው ቃል ነው፥

ቃሉማ ያው ቃል ነው

ትርጉሙም ጉቦኛ አፍቃሪ ነዋይ ነው፥

ብቻ ነጮቹ እንዳይሰሙ አደራ ይህን ነገር

አድርገውን የለ የኤድስ መገኛ አጉር ፥

ለግብረሰዶሙ ሃጥያታቸው ቅጣት

ከላይ የወረደው የተላከው መቅሰፍት ፥

ለኛ መጣ እንዳይሉ አፍረት ቢይዛቸው፥

ባፍሪካ ዝንጀሮ ላከኩት አምጥተው ፥

አንዴ ስሙ አያምርም ስም የለውም ብለው።

ለስም ልጠፋቸው እንዳይመቻቸው ፥

ብቻ አሁንም ልጄ ይህ እንዳይደርሳቸው፥

አሉና አስረዱኝ ያልገባኝን ነገር ፥

ሙስና ቫይረስ ነው ብዬ ስደናገር ፥

ቫይረሱ ነው አሉኝ አውራው የደም ካንሰር

አዎ ቃሉማ ያው ቃል ነው።

                   በ ሳ . አ