አይሆንብንም ሞኝነት ?
|
ብርሃን ፈንጣቂ መቅረዞች አገኘን ብለን አገኘን የጨለምተኝነት ኑሮ ከእንግዲህ ይበቃል ብለን የተስፋችንን ሙጣጭ ዛሬም በተስፋ አዳብለን አዘገምን ስንል ተነሳን አበጀን ስንል ዘየድን የነገ ብርሃን ጠቋሚ ታየልን ስንል ውጋጋን እንደ ጤዛ እየረገፈ ለፍሬ ሳይለው ራዕያችን..... ስንት ዘመን እንደኖርን ..... ስንት ግዜ እንዳሳለፍን..... ዳግም ዛሬም እንቀር ይሆን ? የተስፋ ጭንጋፍ ታቅፈን?
የህብረት ማሳችን ሰብል የአንድነት ዘራችን አዝመራ አበበ ስንል አበበ ...ደረሰ ስንል ጎመራ... አደገ ስንል አደገ..አፈራ ስንል አፈራ ዛሬም ዳግም ያለ ፍሬ እንቀር ይሆን እንደባከን? የተምች ትራፊ እንጭጭ የመከነ ፍሬ ታቅፈን .. እንቀር ይሆን? ......እንደባከን...... አልያማ ... በገቢረ ተስፋችን ዋዜማ .... ትንቢተ ምክነቱ ሲሰማ የብርሃን መቅረዛቱ አበጁ ያልናቸው ....አቤቱ እንደ አባይ የአረብ ነጋዴ በንዋይ ሰነድ ሲሟገቱ እየሰማን እያየነው ! ገበናችን ጸሃይ ሞቆት ስለ አደራ ብናወራ አይሆንብንም ጅልነት? ስለ ተስፋ ብናወራ አይሆንብንም ሞኝነት?
|