Poems                                                 ግጥም

  Back Home      Articles          Poems           News              Jokes               Email Us

        THIS WEBSITE IS CURRENTLY BLOCKED IN ETHIOPIA

             
ምስጋና አይበቃሽም

                                       
                                              
                                 

አዝማች )

ወልደው ካሳደጉሽ ከናት ከአባትሽ
እኔን ብለሽ ወጥተሽ ከሞቀው ቤትሽ
ያን ሁሉ መከራ አብረሽኝ ገፍተሽ
ለዚህ አበቃሽኝ መርኩዜ ሆነሽ
(/
አዝማች )

መከበሬም ባንቺ መኖሬም ባንቺ ነው
የኔማ ሰውነት ያላንቺ በድን ነው
አልብላ ይራበኝ አልልበስይብረደኝ አልጠጣ ይጥማኝ
ብቻ አንቺን ከፊቴ ከጎኔ አይንሳኝ


ለፍቅር የተጎዱ አያሌ ቢሆኑም
እንዳንቺ የተሰው ገጥሞኝ አላየሁም
ምስጋና ይድረስሽ ብየ አልደልልሽም
የጠዋት ጤዛ ነው ምስጋና አይበቃሽም

(
አዝማች )

በመከራው ዘምን በሰቆቃው ወቅት
በፍቅርሽ ተቀኝቶ የልቤ ስር ምት
አላንቺ አልኖር ያለው የኔ ሰውነት
ዛሬ ሲሞላለት ሲደላደል ቀልቡ
ሌላ ክንድ ሊንተራስ ቢመኝም ባሳቡ
ገላ ወረተኛ ማን ይቀየመዋል
ሆድ ሲሞላ ሞልቶ ሆድ ሲጎል ይጎላል

ልቤ ግን አይረሳም አሳዳሪውን
ያን ሁሉ መከራ ያሻገረውን
ያላንቺም ሰው አይለምድ የሌላም አይሆን
አክሊሉን ሰጥቶቻል የክብር ዙፋኑን
የኔን ክፉ አልፈሻል ያንቺን ለኔ ያርገው
ከሌለሽ የለሁም ያለሁት ባንቺ ነው

         በ ሳ. አ