Poems                                                 ግጥም

  Back Home      Articles          Poems           News              Jokes               Email Us

        THIS WEBSITE IS CURRENTLY BLOCKED IN ETHIOPIA

             
ሃገሬ እያለች ይመመኝ

                                       
                                              
                                 

የኔ ቢጤ ወፍ ዘራሹ - ምን ሆንክ ባይ ባይኖረውም
የታመመን መጠየቁ - የዘመድ አዝማድ ወግ ነው ጥንትም
በሽተኛን ማስታመሙ - ሲወርድ ሲዋረድ የቆየው
ታማሚው ሁሌ ሰው ሆኖ - ሃገር ጤና ብትቆይ ነው

ግን እንደ ዛሬው! እንዳ ሁኑ!... አገር ጤና አጥታ ስትሰቃይ
በመርገምት የመሃጸን ፍሬዋ.. ቃሬዛ ወድቃ ስትታይ..
እምን ላይ ሆኖ ሊታመም በሽታው እንኳ ባይጠፋ?
እማን ላይ ሆኖ ሊጠየቅ ምን ሆንክ ባይስ ባይከፋ ?

የኔ ቢጤ ወፍ ዘራሹ - ምን ሆንክ ባይ ባይኖረውም
የታመመን መጠየቁ - የዘመድ አዝማድ ወግ ነው ጥንትም
ግን እንደ ዛሬው! እንዳ ሁኑ!... አገር ጤና አጥታ ስትሰቃይ
በነቀርሳ ፍሬዎችዋ ነቀርሳ ይዟዋት ከደከመች
መታመሚያም ይቸግራል - መታመም ቢችል እንኳ ገላ
መማቀቂያውም አይገኝ - መማቀቁ እንኳ ቢሟላ

ለኔ ብጤ መናጢ እንኳን - ብቻውን ለተፈጠረ
እንደ ጥንቸል ልጅ -አንድ ሆኖ - ነጠላ ሆኖ ለኖረ
መታመሚያው ማገገሚያው - ሃገር ነችና አትታመም
የዘመድ አዝማድ እጦቱ - መቀበሪያውን አይነፍግም

መቼም የዝጌሩ በሽታ - ድሃ ነው ብሎ ላይተወኝ
ሞቴንም ከፊቷ ያድርገው - ሃገሬ እያለች ይመመኝ