ይድረስ ለገነት ዘውዴ ትምህርት ምኒስትሯ

               ከእንግዲህ ትውልድ ሁሉ እርኩሲት ይሉሻል

                                       
                                              
                                 

ወይዘሮ ልበልሽ ክቡርት

አንቱ ልበል አንቺ ገነት

ለሴትማ ለወላድ ወይዘሮ አይደል ወጉ ?

የአጠራር የስም ማረጉ

ግን እንቢ አለኝ ቃሉ

ወይዘሮን ላንቺ መቀጠሉ

ከአለት ጠጥሮ አንጀትሽ

እንዴት ወይዘሮ ልበልሽ ?

የአዛኝ የወላድ ስም ልስጥሽ

ባንቺ ጥሪ! ባንቺ ምሪት! ባንቺ እንቢታ!

በእበላባይ ሎሌነትሽ ለስልጣን ጥማትሽ ርካታ

የጨቅላ ደም እንደ ውሃ ከጎዳና ቦይ ተቀዳ!

ገላው በጥይት ዳታርፎሖቦ ዳግም ለግዞት ተነዳ

አንቺም ለተቀመጥሽበት ወንበር

ለስልጣንሽ እዳ ግብር

የጨቅላ ደም ጭዳ ሰጥተሽ

ዛሬም ክብርት ትባያለሽ

አዬ ክብርት..! አዬ ክብር ...!

አይ ወይዘሮ አዬ ምሁር

ደም ባቀረዘዘው ብእርሽ

ትውልድ በማይረሳው ፊርማሽ

በስመ ኢሃድግ ወ ወያኔ ባርከሽ

የወጣቱን እርድ ፈቀድሽ

ዳግም ስትኮፈሽበት አልከረፋሽም ወንበርሽ

በለጋ ደም የጨቀየው ትንሽም አልሰነፈጠሽ

ዳሩ እለት በእለት ለሚያርድ ሰው

የትኩስ ደም መአዛ እንጂ

ክርፋቱ እንዴት ሊሰማው ?

መሃጸን ፍሬ መስጠቱ የሴት ወጓናውና

አንቺም መቼም በተፈጥሮ ሴት ነሽና

ፍሬ አፍርተሽ የወላድ ወጉ ከደረሰሽ

እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ

እንደ ደራሽ ውሃ ሲሮጥ የልጅዋ ደም በጎዳና

የተመለከትች እናት እንዴት ነው የምትጽናና ?

ለአንድ አፍታ ወላድ ሆነሽ እስኪ አስቢው

ገላው በጥይት ተቦዳድሶ

ደሙ ባፈር ተለውሶ

አፈር ልሶ

ልጅሽን ጎዳና ብታይው

እንዴት ይሆን ስሜትሽ ?

እኮ ምን ይሆን መልስሽ ?

ዳሩ የወላድ አንጀት ቀድሞውኑ መች ኖሮሽ

አዬ ክብርት አዬ ክብር

በደም በጨቀየ ወንበር

ከእንግድህ ትውልድ ሁሉ እርኩሲት ይሉሻል

ይፋረዱሻል ! ይጠይቁሻል!የሞግቱሻል

ገነት ጉዲት ይልሻል

ጉድ ነሽና ይገባሻል

                                          (በሳ.አ)