Poems                                                 ግጥም

  Back Home      Articles          Poems           News              Jokes               Email Us

        THIS WEBSITE IS CURRENTLY BLOCKED IN ETHIOPIA


ኢትዮጵያዊው ኩሩ
 

                                       
                                                                       
 ( በዶክተር ደጀኔ አየለ ተሰማ ኦስትሪያ)

ለማን ይነግሩታል ? ሰሚ የለም ዳሩ፥

ቀብራራ መሆኔን ኢትዮጵያው ኩሩ !

የት ይገባቸዋል _ _ _ !

ገና ከመምጣቴ ይጨቀጭቁኛል፥

ወዲያው ተዋውቀውኝ ከየት ነህ ? ይሉኛል።

አሁን ገጽታዬ መልኬ ጠፍቷ ቸው ነው ?

ወይስ ካፉ ይውጣ ከራሱ እንስማው _ _ _

ብለው ዶልተው ነው ?

እኔስ ማነኝና ቀብራራው አበሻ፥

ኢትዮጵያዊው ኩሩ !

እነግረዋለሁኝ በውል አስረግጬ፥

ከውብ ለምለም አገር መምጣቴን ገልጬ፤

ቢገባው ባይገባው የራሱ ጉዳይ ነው።

ከዚያች ታላቅ ሃገር _ _ _

ከሰው ልጅ መገኛ ታሪካዊት ምድር ፥

የጥንት የመሰረት የአኩሱማይት ኢምፓየር፤

በመምጣቱ ኮራ ተዘባነነብኝ፥

ደረቱን ገልበጦ መልስ መለሰልኝ ፥

ቢለኝ ቢወተውት እኔ ምን ቸገረኝ _ _ _?

ቀብራራው አበሻ ኩሩ ኢትዮጵያዊ መሆኔን ይወቀኝ፤

እሱስ መቼ ካደ _ _ _፥

ያቺን ድንቅ ሃገር አልውቃት መች አለ፥

አሃ ! አለኝ እንጂ ጠልቆ እያስተዋለ፤

እንዲህ እንደዋዛ ከየትም ያልመጣሁ፥

ያልሆንኩኝ ወፍ ዘራሽ መናኛ ከንቱ ሰው፥

ኩሩ ኢትዮጵያዊ መሆኔ ሲገባው።

ግና ሲውል ሲያድር ነገሩን ስረዳው፥

ይሄ ነጫጭባ ሃገሬን ያወቀው፥

እኔ በገመትኩት ባሰብኩበት መንገድ በኩሩነት ሳይሆን፥

ለኔ በማይገባኝ በማይዋጥልኝ፥

በችግረኝነት ቆጥሮኝ እንደለማኝ፥

እንደዚያ ነው ለካ _ _ _!

ገና ከኢትዮጵያ መሆኔን ስነግረው አሃ ብሎ ያለኝ ፥

እኔ መቼ ገባኝ _ _ _ ?

ታድያ እኔ ቀብራራው ባውቅም አመጣጡን፥

አይደለሁም ልል ነው?

ቢያንስ አበሻነቴን ኢትዮጵያዊነቴን

የትም ከጠየቁኝ ነግሬ ባጭሩ

ከጭቅጭቅ ሽሽት ቪደር ሲየኝ እላለሁ።

እሰናበታለሁ።