ባድሜ ቆዳ መልስ ሄደች!
|
ሄደች! _ _ _ ቆዳ መልስ ባድሜ ሄደች! _ _ _፥ የእንቡጥ ወጣቱን ደም ልሳ ፊቷን አዙራ እብስ አለች፤ አላስደፍርሽም ብሎ የሞተላትን አንበሳ፥ በጉያዋ እንኳ እዳያርፍ አስክሬኑን አፈር ምሳ፥ እንካችሁ አለች ቆዳ መልስ የእንቦቀቅላውን እሬሳ፤ በሷው ምክንያት፤ በሷው መዘዝ፤ በሷው ዳፋ፥ ሺ አካላት አፈራርሳ ሺ አበቦችን አስረግፋ እሰይ ስንል፥ እልል ስንል፥ ከቀማኛ ጥርስ ድና፤ እብስ አለች ባድሜ፥ ወንበዴ አገኛት እንደገና፥ ቤዛ ከፍሎ እስትንፋሱን ከቀማኛ የታደጋት፥ ለዛ ለምስኪን ወንድሜ አልኩኝ እኔስ ይብላኝለት _ _ ይብላኝለት _ _ _ _ _ _ " ጋት ስንዝር እንዳትነካ የሃገሬ ዙሪያ ድንበሯ " የሚለውን ውርሰ ቃል የአበው ጀግኖቿችን አደራ፥ የሙጥኝ ብሎ አጥብቆ እሱም ታሪክን ሊሰራ፤ ነበር ሃሳቡ ያ _ _ _ኘ ወንድሜ፥ ክተት ሲሉት _ _ _ ባድሜ። የጥይት ኪኒኑ አንበሳ _ _ _፥ የዛ የመይሳው ካሳ፤ አቻ የጠፋለት ወኔው ታሪኩ ዛሬም እንዲታደስ፥ የጥበበኛው መሃንዲስ የምኒሊክ ካርታ እንዳይፈርስ፤ የአባ መላ፥ የነአሉላ፥ የነባልቻና፥ የነአብዲሳ _ _ _ ሠራቸው እንዳይደበዝዝ ገድላቸው እንዳይረሳ፥ ሃገሩም ዳግም በድል ታሪክ በክብር እንድትወሳ፥ ብሎ ነበር የዘመተው ያ ለጋ ምስኪን ወንድሜ፥ ተደፈረችን ቢሰማ ዛሬ ኮብላይዋ _ _ _ _ ባድሜ፥ አፈሬ ብሎ አትነካም እኔ እያለሁኝ በቁሜ፥ ብሎማ ነበር ያ ጀግና በእሸቱ የጠወለገው፥ ዛሬ ነገር ተበላሽቶ ይብላኝለት _ _ _ _ የሚባለው አዎ ይብላኝለት _ _ _ ፥ ሄደች ! _ ባድሜ ሄደች _ _ _ቆዳ መልስ፥ የእንቡጥ ወጣቱ ደም ልሳ ፊቷን አዙራ አለች እብስ። _ አያሳየው የለ ግዜ አያሰማው የለ ጆሮ፥ የተገላቢጦሽ ሆኖ ዛሬ ሁሉም ተቀያይሮ፤ በእምዬ ምንሊክ እልፍኝ ጉግ ማንጉጉ ሁሉ ገብቶ፤ እንካችሁ አለ መሬቷን፥ እንቢኝ! ለሃገሬ ቀርቶ፤ ሰጠ ባድሜን ሳያቅማማ ገጸበረከት አቃረባት፥ ለዚያውም ለተደቆሰ፥ ለተንበረከከ ጠላት፥ አያልቅባቸው ጉዶች _ _ _ ከሃዲ የብብት እሳቶች _ _ _ ዛሬም ከእድሜው ባይማር፥ ባንዲራን ጨርቅ ያለ አፋቸው፥ "ከአፈሩ አይደለም ቁምነገሩ" ይላሉ አሉ ጉድ እኮ ነው! የአፈርን ብናኝነት ብቻ ተራ አቧራነቱን አጉሉተው _ _ _ ጉድ እኮ ነው! ከአፈር እንጂ ከመሬቱ ፥ የዜጋ ማንነት ቁርኝቱ ፥ ሌላማ ምን ሊኖር ከቶ ? _ _ _ የዜጋ የሕዝብ መታወቂያ፥ እትብቱ ከተዋሃደው ከአፈሩ ከምድሩ ወዲያ፤ ወርቀትማ ይጠፋል _ _ _ _ ፥ 3 ሺህውን ገጽ ቀደው 3 መቶ ሲ^ያረጉትም ሆኗል፥ እንዳስዋሹትም ዋሽቷል እንደጻፉበትም ተነቧል። አፈሩ እንጂ ቁምነገሩ ፤የሕዝብ የዜጋ ክብሩ፤ አይደለዝ፤ አይሰረዝ፤ አይቆረጥ፤ አይቀነስ፥ እንደ ወረቀቱ ታሪክ ዘገባው አይደመሰስ፤ መች ውሸት ያውቃል አፈር፥ መች እንደጻፉት ሊቀላብጥ፤ ሉሲን መሳይ እማኝ ጠርቶ ዋሾን እንጂ የሚያጋልጥ ፤ ለይህም አይደል መጠላቱ ፥ ከዋሾ አልውልም ማለቱ፤ አፈርን ያህል ክቡር ነገር ለወንበዴ መሰጠቱ። እንደ ዳግማ ተንሳይ አክፋይ፥ እንደ ገና ስጦታ ዕቃ፥ አገርን ያህል ክቡር ነገር ለሃራጅ ሺያጭ የበቃ፤ ለይህ እኮ ነው መጠላቱ፥ አፈር አልዋሽም በማለቱ ፤ እናማ ሄደች _ _ ሄደች ባድሜ ሄደች _ _ _ የእንቡጥ ወጣቱን ደም ልሳ ፊቷን አዙራ እብስ፥አለች ። እኔም አልኩኝ ይብላኝለት _ _ _ _ _ ባድሜ ላይ ለተሰዋው ለዚያ ጀግና ምስኪን ወጣት። እስኪ እናተ የምድር ጉዶች ይህን ብቻ መልሱልኝ፥ የአፈር የደም ገበያውን አዋዋሉን ግለጹልኝ የባድሜውን ገድለ ድል በደም የተከተበውን፥ እንደሸቀጥ ተምናችሁ ስትቀበሉ ዶላሩን ፥ ለመሆኑ የነፍስ ዋጋ በስንት ሂሳብ ቢሰላ ነው ? ሬሳው ቆዳ መልስ ሆኖ ባድሜንም ያጣነው፤ እንግዲህማ _ _ _ የክቡር ህይወቱ ዋጋ ሲሳይ ከሆነ ለኪሳችሁ፥ የሟቹስ ታሪክ እልባት፥ መቋጫው ምን ይሁን አላችሁ ? ዳሩ ለመበጣጠስ እንጂ ለታሪክ ቁጭት መች ቆማችሁ። ይብላኝለት ለዚያ ጀግና _ _ ድሉ ሃራጅ ለተሸጠው፥ የደሙ ዋጋ ጥሪት ሆኖ እጉም ጅቦች ኪስ ለገባው፤ ይብላኝለት _ _ _ _ _ _ _ እናተው ክተት ብላችሁ እናተው አዝምታችሁት፥ ቀዳሚ አግሺም ሆናችሁ በሞቱ ማግስት ድል ብስራት፤ በሱ መሞት፥ በሱ ህይወት፥ አነሰና መቆማችሁ፥ ዛሬ በድሉ ጀርባ በሬሳው ላይ ፈርማችሁ፥ በደም የራሰውን አፈር ባድሜን ለጠላት ሰጣችሁ፥ ዘር ንግዳችሁ ቢቀዘቅዝ ደግሞ ወደ ደም ዞራችሁ ከእንግዲህማ ምን ሊባል? _ _ከዚህስ በላይ ምን ሊመጣ ? በበላኤ ሰብ አንጋቾች የጀግና ሞት ሃራጅ ሲወጣ፥ በላኤ ሰብ አንጋቾች የጀግና ሞት ሃራጅ ሲወጣ፥ እናማ፥ ሄደች ባድሜ ቆዳ መልስ፥ የእንቡጥ ወጣቱን ደም ልሳ ፊቷን አዙራ አለች እብስ። የእንቡጥ ወጣቱን ደም ልሳ ፊቷን አዙራ አለች እብስ። የዚህች ግጥም መታሰቢያነት በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ሕይወታቸውን ላጡናኘ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው የኢትዮጵያ ውድ ልጆች ይሁንልኝ ገጣሚው
|