Poems                                                 ግጥም

  Back Home      Articles          Poems           News              Jokes               Email Us

        THIS WEBSITE IS CURRENTLY BLOCKED IN ETHIOPIA


የውግ ካርታ ቁማር !
 


 

                          ላጥ፤ ፐወዝ፤ ገልበጥ፥

 ቆረጥ፤ ደግሞ ጠ _ጠ ጥ _ ጠ ጠ _ ጥ

 ቁማሩ ሊደራ ካርታው ተፐወዘ፥

 ቆርጩ አንዷን ካርታ ማርጦ እየመዘዘ፥

 ለባለ መደቡ መለሰ ሌላውን፥

 ውጉን በአይኑ እያየ የጀርባ ንባቡን፥

 ቀጠለ ቁማሩ _ _ _

 የውግ ካርታ አኪሩ፥

 መደብተኛው በላ ደገመ አሁንም፥

 ኪሱን አሟጠጠ ቆራጩ አልቀናውም።

 አሁንም ቆራጩ ውግ ካርታ መረጠ፥

 መለሰ ካርታውን ለመዳቢው ሰጠ።

 ላጥ ፤ ገልበጥ ፤ ቆረጥ፥

 ደግሞ ጠ ጠ ጠ ጠ ጥ፥

 አድርጎ መዳቢው ቁማሩን ቀጠለ _ _ _

 ውጉን እያሰላ ቆራጩን አቄለ፥

 የቆራጩን አኪር በድን ያደረገው፥

 የተወጋው ካርታ የጀርባው ንባብ ነው።

 የጀርባ ንባቡን _ _ _

 የውግ ካርታ አኪሩን _ _ _

 ጥበቡን ያጤነ፥

 አዲስ ቆራጭ መጣ ምድር ቁና ሆነ።

 በለመደው ዘዴ መዳቢው ሊቀጥል፥

 አዲሱንም ቆራጭ በውግ ካርታው ሊያቄል፥

 ላጥ፤ ፐወዝ፤ አርጎ ካርታውን ቢያቀብል፥

 ይህ አዲሱ ቆራጭ ፥

 የውግ ካርታ አጋላጭ፥

 አልበላም አለ በውግ ካርታ ቁማር፥

 ባለ ውጉ ካርታ ባዲስ ካርታ ይቀየር፥

 ብሎ አዲሱ ቆራጭ አዲስ ካርታ አውጥቶ፥

 እሽጉን ፈታቶ _ _ _

 ላጥ ፐወዝ ገልበጥ ፥

 ደግሞ ጠ ጠ ጠ ጠ ጥ

 አድርጎ ፐወዘ፥

መደቡንም ያዘ።

 ቆራጩ መድቦ መዳቢው ቢቆርጥ፥

 ጦር ሳበና አረፈ አኪሩ ሲለወጥ፥

 አሁንም በጦሩ አልሆንልህ ቢለው

 ከአዲሱ መዳቢ መጫወቱን ተወው

 የበፊቱን ቆራጭ በድጋሚ ጠራው

 አዲሱን ካርድ ትቶ

 ዳግም የውግ ካርዱን ከሠርቻ አንስቶ

 ላጥ ፐወዝ ላጥ፥

 ደግሞ ጠ ጠ ጠ ጠ ጥ፥

 አድርጎ ፐውዘ ፥

 አሁንም ቆራጩ ውግ ካርታ መዘዘ፥

 መለሰ ካርታውን ለመዳቢው አስያዘ፥

 መዳቢም መደበ ውጉን እያሰላ፥

 አሁንም ደጋግሞ ቆራጩ ተበላ።

 ውጉን ካርታ እያየ ደጋግሞ የሚስበው

 ቆራጭ የሚበላው ለካስ ሆን ብሎ ነው ፥

 ከመዳቢው ጋራ የደም ውል አስሮት ነው።

 አሁንም ደጋግሞ ውግ ካርታ መረጠ፥

 መለሰ አቀበለ ካርታውን ለመዳቢው ሰጠ።

 አዲስ ቆራጭ መጥቶ ካርታው እስኪለወጥ፥

 ቆራጩ መድቦ መዳቢው እስኪቆርጥ፥

 ያጋብስ መደብተኛው ይሰብስብ ጥሪት፥

 እስኪተፋው ድረስ አኪር ሞቶበት።