News                                                      Archive

Back Home               Articles              Poems           News              Jokes               Email Us


 የያራው-ኩታራ


ያ የማዳበሪያው ጎተራ...
የፍጋ --ፍጉ ባላዝመራ...
ያራ ......

የልማት አርበኛ የሰራ:
ሰው ጠራሁ ብሎ ኩታራ:
የደም ባለ እዳ ቢጠራ:
ያ የማዳበሪያው ጎተራ:

እቢኝ አለን እንጅ  ዜጋ ወጥቶ:
ገዳይ ሲሸለም ተቆጥቶ...:
እጀ ሙቅ ቀርቶ ለወንጀሉ:
የልማት ጀግና ነህ መባሉ:

እንዴት ተደርጎ ማለቱን?
የወገን ቁጣ ግለቱን....
ሰማን የኖርዌዪ ሙግቱን!
የዜጋን ...ውሎ የትናቱን

ፍጋ -ፍግ ከሰው ከበለጠ..!
ለገዳይ ኒሻን ካሰጠ፡

እንግዲ ምን ሊጠቅም ያራ..?
ልማቱስ ለማን ምን ሊሠራ..?
የሰው ልጅ አልቆ በካራ..!
በአረመኔ እጅ በኩታራ ..!
ከሳሽ ቢጠፋ የሚሞግት..፡
ጭራሽ ገዳዩን ይሸልሙት..?
የልማት አርበኛ ይበሉት..?

ፍጋ - ፍግ ከሰው ከበለጠ..!
ለገዳይ ኒሻን ካሰጠ..!

እንግዲ ምን ሊጠቅም ያራ?
ልማቱስ ለማን ምን ሊሠራ?
ነፍሰ ገዳዩን ኩታራ፡
ከፍ ከፍ አርጎ ያኮራ፡
ደሞ ....የምናባቱ..ያራ!
ፍግ የፍግ ወዳጅ ደንቃራ!!!
ደሞ ....የምናባቱ..ያራ፡