News                                                      Archive

Back Home               Articles              Poems           News              Jokes               Email Us

ል  ጠ

ተስፋዬ አካለ ወለድ
ከኮልራዶ
 
የጠ/ሚ መለስ የ 25 ደቂቃው የፈንጂ ወረዳ ቆይታ


ጠ/ሚ መለስ ከቢቢሲው ጋዜጠኛ ጋር ያደረጉትን የ24 ደቂቃዎች ቆይታ በርካታ ኢትዮጵያውያን እንደ ተከታለው እገምታለሁ!!   ላለፉት 14 አመታት ከታዞ አዳሪ የድርጅትና የመንግስት ጋዜጠኖች ጋር በጥናት የተዘጋጀ የጥያቄና መልስ ድራማ ሲተውኑ የቆዩት የኢትዮጵያው ጠ/ሚ  በሥልጣን ዘመናቸው ውስጥ ሁሉ እንዳሁን ፈታኝ ፤ አስጨናቂና ውጤቱም አስከፊ የሆነ ቃለ መጠይቅ እንዳላደረጉ ወይም እንዳላገጠማቸው ያለኝን እምነት ብዝዎች እንደምትጋሩኝ አልጠራጠርም፡፤የፈንጂ ወርዳ የሚለውን በአደጋ ተምሳሌነቱ  በራሳቸው በ/ጠሚ መለስ ተዘውትሮ የሚጠቀሰውን  አገላለጽ  ለዚ ጽሁፌ መነሻ ይሆነኝ ዘንድ የመረጥኩበት አብይ ምክንያትም ይህንኑ እይታዬ ለማድመቅ ማሰቤ ነው።

ስለ ጠ/ሚኒስትሩ  ችሎታ! ስለ ነገር አዋቂነታቸው ! ባጠቃላይ ስለ ልዩ ችሎታቸው ብዙ ብዙ ተብሎላቸዋል! ከቅርብ አመታት ወዲህ ደግሞ  አቶ መለስ እንዲህ አሉ፡ አንዲህ ተናገሩ የሚሉ አስቂኝ የፈጠራ ወጎች በአፍቃሪ ወያኔ አካላት  እይተጠረቀላቸው እንደነበር  ሳትሰሙ እንደማትቀሩ እገምታለሁ! ፤ አቶ መለስ እንዲህ አሉ፤ እንዲህ ተጠይቀው እንዲህ መለሱ፤ በሚል በጥያቄና መልስ ዘይቤ የሚወራላቸው ነገር እየበዛ ሲመጣም እውን እኚህ ሰው እንዲህ ቀልድ አዋቂ ናቸው? ወይስ የበትረ ስልጣኑ ሞገስ ይሆን የረባውንም ያረባውንም አባባል አስቂኝ ያደረገው? የሚለው ጥያቄ በዚህ ጽሁፍ አቅራቢ አይምሮ ሲጉላላ ቆይትዋል። እውን እንደ ሚወራው ቀልዱና ወጉ ሁሉ ከሳቸው አንደበት የወጣ ከሆነ   እውነትም እኝህ ሰው  የዲሞክራሲው ዘመን አለቃ ገብርሃና ሊባሉ ይገባቸዋል ያሉም አሉጠፉም። ይህን ሁሉ ያልኩት ወዴት ለመንደርደር እንደሆነ ይጠፋችኋል ባልልም ! መግቢያውን አርዝሜ  ዋናው የጽሁፌ  አላማጋ ሳልደርስ ትንፋሽ አጥሮኝ በመንደርደር ጀምሬ በመንደርደር እንዳልጨርስ በቀጥታ ወደ ነጥቤ ላምራ!!

አቶ መለስ ከቢቢሲው ጋዜጠኛ ጋር ባደረጉት ቃለመጠየቅ፡ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የሞራል ድቀት እንደደረሰባቸው በገሃድ አይተናል፡፤! ቃለ መጠይቁ እንደ ግለሰብ ግለሰባዊ ባህሪያቸውን ያስገመተ! እንደ መንግስት መሪነታቸው  ደግሞ መንግስታቸው ምን ያህል ኢዲሞክራሲያዊና ኢ-ፍትሃዊ እንደሆነ በገሃድ ያሳየ ነው!

24 ደቂቃ በቆየው ቃለ መጠይቅ ውስጥ ለጠ/ሚ መለስ እጅግ በጣም ፈታኝና አስጨናቂ የነበሩትን ሁነቶች አለፍ አለፍ ብለን እንመልከት! በዚህ ጽሁፍ አቅራቢ እምነት  ጠ/ሚንስትሩን ያሰደነገጠውና  ለመጀመሪያ ግዜ ሚዛን ያሳተው የመጀመሪያ ፈተና የተከሰተው በሁለተኛው ደቂቃ አጋማሽ ላይ ነበር! 

 ጠ/ሚሩ የውጭ ታዛቢዎች ስለምርጫው የሰጡትን  አስተያየት ሲገልጹ -የምርጫው አጠቃላይ ሂደት  በሁሉም መልክ ነጻ ግልጽና ዲሞክራሲያዊ እንደነበር የውጭ ታዛቢዎች በአንድ ድምጽ የመሰከሩለት ምርጫ ነበር ብለው ሳይጨርሱ !! 25 የጣር ደቂቃዎችን ያስቆጠራቸው ጋዜጠኛ  አባባላቸውን ተቃወመ።

ጋዜጠኛው የጠቅላይ ሚኒስትርን አባባል ሃሰትነት በማስረጃ እያጣቀሰ በማረጋገጥ  ለጠ/ሚ መለስ በተዘዋዋሪ ማስተላለፍ የፈለገው  መልእክት አንድና ግልጽ ነበር፡፤ " ክቡርነትዎ ለርስዎ ያለኝ ክብር እንደተጠበቀ ሆኖ ነገር ግን ውሸታም ነዎት!" ነበር መልእክቱ፡
የጠ/ሚ መለስ  የመደናገጥና የእፍረት ስሜት በከፊል መነጽር ከሸፈነው ፊታቸውም ላይም ቢሆን መነበብ የጀመረውም በዚሁ ቅጽበት ነበር፡፤

በመቀጥልም በአልሞት ባይ ተጋድይ አይነት ስሜት ቀደም ሲል የሰጡትን የምርጫው ሂደት በጠቅላላ ትራንስፓረንትና ፌር ነበር ሲሉ የውጭ ጋዜኞች ያለምንም አሉታዊ መገለጫ መስክረዋል የሚለውን ሃሰተኛ  አስተያየት ወደ እውነታው በማስጠጋት..የውጭ ታዛቢዎቹ "እስከ ምርጫው ቀን ድረስ" የነበረው ሁኔታ ጥሩ እንደነበር መስከረዋል ብለው መናገራቸው  ጭራሹኑ ሆን ብለው  መዋሸታቸውንና  ከሆነ ሆነ ከተነቃም ይቀራል አይነት ከአንድ ጠ/ሚር የማይጠበቅ የማጭበርበር ሙከራቸውን ከማጋለጥ በስተቀር ምንም የፈየደላቸው ነገር አልነበረም።

በርግጥ እንደ ሌላው የሙያ መስክ ሁሉ  የፖለቲካው አለም ሰዎችም  ሊያክብሩት የሚገባ የሙያ-ሥነ ምግባር ብሎ ነገር ብዙም የማይታወቅና እንቅስቃሴዎቹ ሁሉ የተቻለውን ዘዴ ሁሉ ተጠቅሞ የህዝብን ይሁኔታ ለመግኘት የሚደረግ የጥሎ ማለፍ ግብግብ የበዛበት መሆኑ ግልጽ ነው። ይሁንና   የመጨረሻውን የሥልጣን እርከን ተቆናጦ በሃገር መሪነት የተቀመጠ እንደ ጠ/ሚ አይነት ሰው እንቅስቃሴ  የሚገመገመው ግን በፖለቲካ ሞያተኝነቱ ሳይሆን በሃገር መሪነቱ ሊሆን ግድ ይላልና  በጠቅላይ ሚ/ር ላይ የታየውም የመዋሸት ሙከራና በተከታታይም ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስ መስጠት ያለመቻላቸው  አሳፋሪነትም በያዙት ወንበር መጠን ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው  ነው እላለሁ፡፤

አለ መታደል ሆኖ  ከስልጣን ዘመናቸው በህዋላ ያላቸውን ህይወት ኪትዮጵያ ህዝብ ጋር ያሳለፉ መሪዎች ሊኖሩን ባይችሉም   ከውጭው አለም ልምድ ማየት እንደምንችለው የሃገር መሪዎች በስልጣን ዘመናቸው የሚያደርጉት እንቅስቃሴና በተለይም የሚታይባቸው የባህሪ ግድፈት ምን ይሃል ተሰሚነት እንዳለውና ጎልቶም እንደሚወጣ መረዳት የሚቻል ይመስለኛል፡፤ በዛውም አንጻር ከሥልታን ከወረዱ በህዋላ ያለው እንቅስቃሰያቸው ደግሞ የማንንም ቀልብ እንደማይስብ ብዙም ወደ ህዋላ ሳንሄድ ከፕሬዘዳንት ክሊንተን ታሪክ ማስታወስ  የሚቻል ይመስለኛል፡፤ እዚህ ላይ ላስመርበት የፈለግኩት ነጥብ በሃገርና በህዝብ መሪነት የተሰየሙ  መሪዎች የክብራቸውም ሆነ የተሰሚነታቸው ብሎም የያንዳንዷ እንቅስቃሴያቸው ግዝፈት አብይ  ምክንያት፡፤ከወንበሩ ጀርባ  ያለው ግዙፉ ህዝብ ነው፡ የሚለውን እውነታ ነው፤ የአቶ መለስ ግድፈት  ጎልቶ እንዲታይ የሚያደርገውም  በኢትዮጵያ ህዝብ ስም በተቀመጡበት ወንበር ላይ ሆነው መዋሸታቸው ነው፡፤

                                                                                                                        ወደ ቀጣዩ ገጽ