እናትዎስ እንኳን ሞቱ! …
|
በሠለሞን (ከU.K) እናትዎስ እንኳን ሞቱ! … ዳግም ፍሬ ሳያፈሩ፣ አንድ ነቀርሳ ተክለዋል… የሚበቃ ለሀገር- ምድሩ፣ ግና!! ...... በኔ ግምት...! በኔ እሳቤና ምልከታ፣ እርስዎን ሊወልዱ ማልነበር..? የተላመኑት ከጌታ! መልካም ሲሆን እንጂ ፍሬ!! ለወላጅም
የሚያኮራ፣ መች የትቢት! መሰሪ ሊቅ? ጭንጋፍ የተንኮል ደብተራ! ለፍሬ ባይለው ባያድለው! የናትዋ ተማጽኗቸው፡ በፍጡር ደም የሚታጠብ የግፍ -አጋፋሪ ሰጣቸው!! አዎ!!!!!...................... እናትዎስ እንኳን ሞቱ! … ዳግም ፍሬ ሳያፈሩ፣ አንድ ነቀርሳ ተክለዋል… የሚበቃ ለሀገር- ምድሩ፣
እንኳን ሞቱ!! እንኳን ሞቱ… ቆመው ከሚያዝኑ በልጃቸው ኖረው ከማልቀስ በፍሬአቸው…አፈር ምስጡ ነው ሚሻላቸው
ምንነትዎም ከማይለየው...ከርስዎ አይነቱ
አካይስት!! አዎ!!!!! እናትዎስ እንኳን ሞቱ! … ዳግም ፍሬ ሳያፈሩ፣ አንድ ነቀርሳ ተክለዋል… የሚበቃ ለሀገር- ምድሩ፣ |