News                                                      Archive

Back Home               Articles              Poems           News              Jokes               Email Us

ሸረሪቷ

ሸረሪቷ

 

አየሃት...? አየሃት...? አንተ የኔ ጎረቤት፡!

ይህቺን ሰለክላካ መርዘኛ ሸረሪት....!

እያት...! ስትታከክ ይህንን ግድግዳ..!

ተአፈሩ አፈር  መስላ ስትፈልግ ቀዳዳ፡

አየሃት...? አየሃት...? አየሃት ይቺን ጠንቅ

እይልኝማ አንዴ! ድርዋን ስታጥብቅ፤

ተንጠላጥላ ወርዳ መርዟን ልትፈነጥቅ!

እያት! እስኪ እያት! ስትንሿከክ እያት

እውን እንዲህ የሚስብ ቅል አላት ሸረሪት?

ተአፈር አፈር መስላ ነድፋ የምትጥለበት?

ወይስ ለመርዘኛም መርዘኛ አምላክ አለው?

አካል አልባ እስትንፋስ  በል! አድርግ የሚለው?

ታዲያስ... ጎረቤቴ ! ዝም አልክሳ ምነው?

እሷም እንደ እንሥሳ ልታሳዝንህ ነው?

በል ስጠኝ ጭራሮ ልበጣጥሰው ድሯን!

አንተም አፈር አቡካ ድፈን ቀዳዳዋን ፤

ሆደ ባሻ አትሁን ሸረሪት ገዳይ ናት!

መርዟን ሳትፈነጥቅ በጭቃው ለስናት፤

እኝክ ምስር ተፍቶ መርዟን የሚረክሰው

የሷው ዘር ነውና ብንሞትም ግድ የለው!

እና ጎረቤቴ!  ሰኞን እንዳንሆን.........

እኔም ድሯን ላጥፋ አንተም ሽንቁር ድፈን!!