News                                                      Archive

Back Home               Articles              Poems           News              Jokes               Email Us

??? ?????

ማነው የሚታመን?


ከሰው በላይ ማነው የሚታመን ለሰው
ከህሊናስ በላይ የሰው ዳኛ ማነው! 
ስውም እንደ እንሰሳ ስሜቱ ከነዳው
ከከብት ይለይ ዘንድ ህሊናው ካልረዳው
የሰው ሰውነቱ ክብሩ ምኑ ላይ ነው?
መታመንስ ለማን? እምነትስ ምንድነው?

ባለ ሁለት ጸጉር ምራቁን የዋጠ
ከሰው መሃል በሰው ታይቶ የተመረጠ
ትዝብተ ህይወቱ እድሜው ተገምቶ
ከሰው መሃል በሰው ለቁምነገር ታጭቶ
አመዛዛኝ ፍጡር አዋቂ ነው ያሉት 
በተግባሩ ዘቅጦ እረክሶ ሲያገኙት
እድሜው ሳይደግፈው የንጨት ሽበት ሲሆን 
ታዲያ ከሰው በላይ ማን ለሰው ይታመን!

አዋቂ ነው ያሉት ቅሌት ከወረሰው !
ማነው የሚታመን? ከሰው መሃል በሰው! 
ከፍ ከፍ ሲያደርጉት ተልከስክሶ ሲገኝ !
የኔ ያሉት ወገን የያዙትን ሲመኝ....!

ስሜቱ እንደ እንሰሳ እንደ ከብት ከነዳው!
ታዲያ ማን ይታመን ከሰው በላይ በሰው ?
የንጨት ሽበት ሆኖ እድሜው ካልደገፈው?
የሰው ሰውነቱ ክብሩስ ምኑ ላይ ነው?
ከከብት በላይ ሊሆን ያበቃው ምንድነው?

ሰው ሊከበር በሰው !
ሰው ሊታመን በሰው !
አይበቃ ከሆነ ከዘቀጠ - ግብሩ!
ምኑ ነው እውቀቱ? የቱ ላይ ነው ክብሩ?
ከእንሰሳ መሻሉስ ምን ይሆን ሚስጥሩ!

ሰውን እንደ እንሰሳ ስሜቱ ከነዳው!
መታመንስ ለማን? እምነትስ ምንድነው?
ከህሊናስ በላይ የሰው ዳኛ ማነው?
ማነው ከሰው በላይ የሚታመን ለሰው?
ስሜት እንደ እንሰሳ ሰውንም ከነዳው!