News                                                      Archive

Back Home               Articles              Poems           News              Jokes               Email Us

የማስታወቂያ ሚኒስትሩና ባርቴንደሩ

 

የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አቶ በረከት ስምኦን በግንቦት 7 ምርጫ በላሊበላ ምርጫ ጣቢያ ተወዳዳሪ ሆነው ቀርበው መሸነፋቸው ይታወሳል፡ ይሁን እንጂ የምርጫ ቦርድ መሸናፋቸውን አረጋግጦ ለአሸናፊው ግለሰብ ፈርሞ የሰጠውን ማስረጃ ወደ ጎን ብሎ አቶ በረከት  ምርጫው ተጭበርብሯልና ይደገምልኝ  በሚል ያቀረቡትን ክስ በመቀበል ምርጫው እንዲደገም መወሰኑም ይታወሳል፡፤
ይህን የምርጫ ቦርድን ውሳኔ የተቃዋሚው የቅንጅት ተወዳዳሪ የነበሩትና አቶ በረከትን ያጨነፉት አቶ .......በመቃወም በድጋሚ ምርጫው እንደማይሳተፉ በማሳወቅ ይወጣሉ፡፤ አቶ በረከትም ብቻቸውን ተወዳድረው አሸናፊ ሆኑ ተባለ፡፤

አቶ በረከት ለድጋሚው ምርጫ ሽር ጉድ ሲሉ የሚታፈነውን ሲያሳፍኑ የሚደለለውን ሲያስደልሉ ብቻ የሚቻለውን ብቻ ሳይሆን ያማይቻለውንም ሲያስችሉ ሰንብተው ብቻቸውን ተወዳድረው ብቻቸውን አሸንፈው ወደ አዲስ አበባ  እንደመጡ አንድ ሆቴል ይገቡና አገር በቀል የሚሏትን የመሎቲ ቢራ አዘው አንዷን በቁማቸው ይልኳታል። ተንፈስ ካሉ በኋላም።ባንኮኒውን በጠርሙሲ ኳ ኳ አድርገው

"እባክህ ይህቺን ቢራ ድገመኝ " ይሉታል፡

አስተናጋጁም ቀልደኛ ቢጤ ነበርና "  ክቡር ሚኒስትር ቢራውም ተጭበርብሯል እንዴ ይደገም ያሉት ? " በማለት በነገር ወግቷቸዋል።

                                                                                                                                                             አንባቢ ምንጭ ጠቅሶ የላከልን