|
በአስራደው (ፓሪስ/ፈረንሳይ)
የምሁር መሃይም ተባይ አላዋቂ፤
የመሃይም ኩፍስ አስመሳይ አዋቂ ፤
ያአንበሳ ልክስክስ ልፋጭ የሚያላምጥ ፤
የጅብ ባለግዜ ታፋ መራጭ ከሽንጥ
የቁራ እርግብ መሳይ ሰላምን አብሳሪ ፤
የፈረስ አዝጋሚ የግመል ሰጋሪ.፣
የባዕድ ባለቤት የነባር ባይተዋር፤
ሥልጡን ሥራ ፈቶ ሞያ ቢስ ሲገብር ፤
ልማድ ሆኖ ቀረ አቀርቅሮ መኖር ፤
በተወለድንበት በኢትዮጵያ ምድር ፤
ያቀረቀረ ራስ ቀና እንዲል ካንገቱ ፤
ተመልሶ እንዲከብር የሰው ሰውነቱ ፤
ከወደቅሽበት ማጥ ካዘቅጥ እንዲያወጣሽ
ዛሬም እንደ ትናት እንዲታደስ ክብርሽ
እምዬ ኢትዮጵያ ጀግና ውለጅ ባክሽ!!
እምዬ ኢትዮጵያ ጀግና ውለጅ ባክሽ!!
|