News                                                      Archive

Back Home               Articles              Poems           News              Jokes               Email Us

የቅኔው እርምት አልገባኝም

 

ከላይ  የተቀመጡትን ሁለት ስንኞች አስመልክተው በአቶ እ.ተ የተጻፈው(ይህን አስተያየትና) በቋጠሮ አዘጃጋጆች የተወሰደውን የእርምት ሂደት አንብቢያለሁ፡ ስለ ፍርዱ ጉዳይ  (ስለ ስንኞቹ አወራረደ) እንዴት እንደሆነ አስቸግሮኛል፡፤ በርግጥ "ደመቀ ስማችሁ" ሊል የሚችለው   ከአነጻጻሪው  ከዝንብ ጋር  እንጂ ሊመላከት የሚችለው   እንደ ባለ ማርዋ  ንብ ደመቃችሁ ስማችሁ ተጠራ የሚለውን እንዴት ሊያመላክት እንደሚችል ሊረዳኝ አልቻለም።

በምሳሌ ላስረዳ.  ስንኞቹ እንደዚህ  ተጽፈው ቢሆን ኖሮ

በግንቦት ጠራራ ንብ ነን ብላችሁ!
ምነው  እንደ  ንብዋ ደም ቀሰማችሁ!          

የግጥሙ ጸሃፊ ንብ ላይ አትኩሮ ስለነበር  ስንኞቹን ለምን ከላይ እንደጠቀሰው እንዳልጻፈው መረዳት ይቻላል፡፤የስንኞቹ  መሰረታዊ ችግር ይህ ነው፡፤ነገር ጊን ከላይ በምሳሌ እንደተጠቀሰው  ተጽፎ ቢሆን ኖሮ ስማችሁ እንደ ንብ ደመቀ የሚለውን ወርቅ  ሊያዝል ይችል ነበር።  የሚነጻጸረው ከንብ ጋር  በመሆኑ፡፤

ነገር ግን ግጥሙ በመሰረቱ ሲጻፍ እንደዚህ ምሳሌ ባለመሆኑ በአስተሳሰብ አወራረዱ እራሱን ቀውስ ውስጥ በመጣሉ የቋጠሮ አዘጋጆች በዚህ ምክንያት  በእርምት ቢያነሱት ይገባኛል፡፤ነገር    ግን እንደ መሰረታዊ አቀራረቡ ከሆነ እንደ ዝንብ ስማችሁ   ደመቀ ይል እነደሆነ እንጂ ከንብ  ጋር የሚያያይዘው ነገር የለም፡፤እንዳለም ብንመለከተው እንደ ዝንብ ስማችሁ ደመቀ የሚል ሲሆን መድመቁ ምኑ ላይ ነው?  ያሰኝ  እንደሁ እንጂ የዝንቦችን ቖሻሻ መውደድ ለመጠቆምና ይህንንም እንደ ድምቀት   ለመመልከት ቢሆን አዲስ የሥእላዊ ድርሰት አስተሳሰብ ከመሆኑም ሌላ ከንቢቱ ጋር የሚያገናኛው ምንም ነገር የለም
ወያኔዎች  እንደ ዝንብ ቆሻአሽ  ላይ ይከመራሉ ሊል ከሚችለውን አዲስ የአማርኛ አጻጻፍ ጋር ፍቅር ባይኖረኝም  መሰረታዊ አሳቡ ግን የወያኔዎች የግፍ አገዛዝ ለመግለጽ መሆኑ እረዳለሁ፡፤

አስተያየተን ለማጠቃለል ያህል፡፤የግጥሙ ደራሲ እነዚህ ሁለት መስመሮች እንዴት ትክክለኛውን  የግጥሙን መል እክት እንዳጨናገፉት ተረድቶ አሻሽሎ እንዲያቀርበው ድጋፌን እገልጻለሁ፡፤ በህይወት ውስጥ እንደሚናልፋቸው አያሌ ነገሮች ሁሉ ጥቂት መሰናክሎችም በርካታ ቀና አላማዎችን ያደናቅፋሉና  ......፡፤           

በሥነ-ጽሁፍና በግጥሞችህም በኩል ለኢትዮጵያ ትንሣዔ የሚደረገው  ተጋድሎ እንዲያብብ ያለኝን ልባዊ ምኞት እገልጻለሁ።

በርቱ እንበርታ!    

     BTafesse
                                


ከቋጠሮ ዝ/ክፍል

ከላይ የቀረበውን አስተያየት ለሰጡን ለአቶ  BTafesse የቅድሚያ ምስጋናችንን እያቀረብን የኛን አስተያየት ከመሰንዘር ተቆጥበን ርዕሱን ለውይይት ክፍት በማድረግ ሌሎች አንባብያን የሚሉትን በዚሁ አምድ ይዘን ለመቅረብ አስበናል፡፤በተለይም ቀደም ሲል እርምቱን የሰጡት አንባቢ እ.ተ የሚሉት እንደማይጥፋ ተስፋ በማድረግ  እንጠብቃለን ፡፤