News                                                      Archive

Back Home               Articles              Poems           News              Jokes               Email Us

ህልም አላሚውና እልም ፈቺው


                          ፍችውን ንገሩኝ

                                     ( በወለላዬ )

መሪው ይመስሉኛል እኚህ አቶ መለስ
ጠቁረው ከሰል ገብተው ልክ እንደዲያቢሎስ
እረጃጅም ቀንዶች በብዛት አብቅለው
እንደራበው አውሬ አፋቸውን ከፍተው
እራስ የሌላቸው ሰዎች ተሸክመው
የሳቸው ጭንቅላት ትልቅ ክምር መስሎ
ከቀጭን አንገት ላይ በታምር ተሰቅሎ
አንድ እጃቸው ቀጥኖ አንደኛው ወፍሮ
ሆዳቸው ወደፊት እጅግ ተወጥሮ
ባካላቸው ዙርያ ቃጭል ተቆጣጥሮ
ያንን እያንሿሹ እያንቀጫጨሉ
መላ አካላቸውን እያጥመለመሉ
ብዙ ሰው ተነጥፎ እየረጋገጡ
አንዳንዱን አንስተው በቁሙ እየዋጡ
አፋቸው እጃቸው በደም ተጨማልቆ
እልፍ አእላፍ ፍጡር ከኍላቸው ወድቆ
ቆመን ያለነውን እንደዛው ሊረግጡን
ትንሽ ሲቀራቸው ደርሰው ሊወጡብን
አንዲት ሴት ልጆችዋን ከኍላ አስከትላ
አንዴ ስትላቸው በያዘችው ዱላ
ያሁሉ አካላቸው ፈራርሶ በመናድ
ወዲያው ተቃጠለ ሆነ ቁልል አመድ
ምን እንደሆን እንጃ ይሄን ህልም አየሁኝ
እስቲ የምታውቁ ፍቺውን ንገሩኝ

 
          ፍቺውማ እንዲህ ነው


                               (   በአብራራው )

ወዳጄ ወለላዬ የሥነ
-ግጥም አምባው -
የህልምህ ትርጉሙ -ፍቺውማ ይህ ነው
ብቻ አለቃ አምባቆም የልም ፍቺ ሊቁ
ማን ፈታልህ ብለው ድንገት ቢጠይቁ
አብራራው መሆኔን አደራ እንዳያውቁ ..
የቅኔ ተማሪ ገና ያልተመረቀ ...
እንዴት የእልም ፍቺ ሚስጥሩን አወቀ ?
ብለው ተቆጥተው ... ቱግ ብሎ ደማቸው
ውጣ እንዳይሉኝ ከደብር ድቁናዬን ገፈው !
አደራ ፍቺዬን በሚስጥር ሸብበው ...!!


እልም እንደ ፈቺው ነው !ይባል እንጂ ቅሉ
ተፈቺው አይደለም - ታላሚው ነው ውሉ
መጻኢ -መከራ -ወይም ራዕይ ሊሆን ...
እልም ሲበረበር ...ትርጉሙ ሲከሸን
አንድም በተቃርኖ በአንጣሩ ይፈታል
አልያም ባአምሳሉ ትርጉሙ ይሰጣል

የልም አለሙ ተባይ ... በአምሳሉ ስንፈታው
በውኑ አለም ምቀኛ ......ሸረኛ ማለት ነው
በእልም አለሙ የሞተ ...የተቀበረ ሰው
የተቃርኖ ፍቺው ....በእውኑ አለም ጥጋብ ነው።

ያንተ የወዳጄ ! የወለላዬ ህልም ....
እነሆ እንዲህ ነው ...በውን ሲተርጎም
የሳጥናዔል ውላጅ ... ያምሳሉ ዳቢሎስ ....
የንጥጥር ፍቺው ...እራሱ ነው መለስ
ባናቱ የፈሉትም ....ረዣዥም ቀንዶች
ሃሳብ ጭንቀት ንዴት ....ናቸው ፍርሃቶች
አፉን ከፍቶ ያለው ...እንደራበው ..አውሬ
በል በል እያለው ነው ..ደም ጠምቶት አጅሬ
እራስ አልቦ ሰዎች ..... የተሸከማቸው
በውኑ አለም ተጠሪ ...ወኪል አምሳያቸው
በረከት ዋለዋ ...እነ አዲሱ ናቸው
የሳቸው ጭንቅላት ለጉድ የገዘፈው
በተንኮል በውሸት ...በክደት ሞልቶ ነው፡፤
አንደኛው ቀጭኑ ጭራሮ ... እጃቸው
ማታለያቸው ነው .... ጦቢያዊነታቸው
እንደዘነዘና የወፈረ እጃቸው ....
በኤርትራዊ ደም ...ለጉድ ተሞልቶ ነው።

በሆዳቸው ዙሪያ የተቆጣጠረው .
የሚንሽዋሽዋው ቃጭል ...የሚያደነቁረው ....
ሆድ አደሩ ካድሬ ያ ሰበርጉማ ነው

ወሩ -እንደገባ እርጉዝ ... ቀፈቱን የነፋው
ከማሌዥያ ባንክ ..... ያኖረው ብር ነው ...
በደም መጨቅየቱ ..አምሳል ነው ፍቺው
ደሙም ያፈሰሰው ...እጁም ያ ቃታው

በተኛው ሰው ጀርባ የሚረማመደው ..
14 አመቱ የመሪ ጉዞው ነው .......
ያቺ እናት ያቺ ሴት !... ልጆች አስከትላ
ያንቆራጠጠቺው ...በያዘቺው ዱላ ....
14 አመትዋ ግፍ .. ቻይዋ ሃገር ናት
ዛሬ አይዞሽ ባዮች ልጆች በዝተውላት
ክንድዋ ፈርጠም ሲል ቅዝምዝሙን ሰዳ
አሸመደመደቺው ይህን ያገር እዳ .......

እንግዲህ ወዳጄ ክቡር ወለላዬ .....
ይህ ነው በኔ በኩል ...ለህልምህ ፍቺዬ

እልም እልም አትበል ...ሲሳይ ነው ! ህልምህ
ፍጹም አትስማቸው ቅዠት ነው ቢሉህ
ቅዠት የነሱ ነው ......አሜን በል ! አይዞህ !!!