(ሆያ ሆዬ -በሶሎሞን ደነቀ) እንኳን አደረሳችሁ!!!




 

አቶ አማረም በጋዜጣቸው የፍርድቤቱን ውሳኔ እንዲህ ሲሉ አውግዘዋል::

———————————————-

የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሴንተርን ንብረት ሰብሮ በመግባት ተቆጣጠረ

“ድርጊቱ አሳፋሪ፣ ሕገወጥ፣ በሰብዓዊ መብትና በፕሬስ ነፃነት ላይ የተነጣጠረ ጥቃት ነው” ኤምሲሲ

(በጋዜጣው ሪፖርተር)

የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ትናንት ሐምሌ 14 ቀን 2002 ዓ.ም. የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሴንተር (ኤምሲሲ) በሊዝ የገዛውንና በፍርድ ቤት እግድ ሥር ያለውን ቤት በኃይል ሰብሮ ተቆጣጠረ፡፡

ኤምሲሲ ድርጊቱን አሳፋሪ፣ ሕገወጥ፣ በሰብዓዊ መብትና በፕሬስ ነፃነት ላይ የተነጣጠረ ጥቃት መሆኑን ገልጻል፡፡

የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ይህንን በሊዝ የተገዛና በባንክ መያዣነት የተያዘ ንብረት የራሱ እንደሆነ በመግለጽ በፍርድ ቤት የአስረክቡኝ ክስ መስርቶ ነበር፡፡ ኤምሲሲ በበኩሉ በፍርድ ቤት አሳግዶ ጉዳዩ ለፊታችን ሰኞ ሐምሌ 27 ቀን 2002 ዓ.ም. ተቀጥሮ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እግዱን እንዳነሳና ከ10 ቀናት በፊት ስለ እግዱ መነሳት የሚገልጸውን የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ኤጀንሲው ለባለንብረቱ እንዲያሳውቅ ቢገልጽም፣ ያለምንም ቅድመ ማሳወቅ የኤጀንሲው ሰዎች ግቢውን ሰብረው የገቡት ከምሽቱ 12 ሰዓት ነበር፡፡

ንብረቱን ለረዥም ጊዜ ሲጠብቁ የነበሩ የኤምሲሲ ጥበቃዎች ተባረው በሌሎች እንዲተኩ ተደርጓል፡፡ የኤጀንሲውን ድርጊት ለመዘገብ በሥፍራው የተገኙ የሪፖርተርና ሌሎች ጋዜጦች ከሥፍራው ሲባረሩ፣ በኤጀንሲው የተመረጡ ሚዲያዎች ብቻ እንዲገኙና ፎቶግራፍ እንዲያነሱ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ የሪፖርተር ፎቶግራፈር ያነሳቸው ፎቶዎች በግዳጅ ተሰርዘው እንዲጠፉ ተደርጓል፡፡

ሚዲያና ኮሙኒኬሽንስ ሴንተር በሳምንት ሁለት ጊዜ በአማርኛና ዘወትር ቅዳሜ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚታተሙት የሪፖርተር ጋዜጦች አሳታሚ ድርጅት ነው፡፡

—————————————–
 

this is Amharic page style